አዘጋጆች





''መጽሐፈ ሲራክ ኢያሱ ሲራክ የተነገረው ነገር ይህ ነው፤ኢያሱ ማለት መድኃኒት ማለት ነው፤ሲራክ ማለት ጸሐፊ ነው፤የኢየሩሳለም ሰው የአልዓዛር ልጅ እኔ ኢያሱ ሲራክ ኢታምልክን ዘጠኙን ሕግጋት በዚህ መጽሃፍ ጻፍኩ። '' 

ይህ መጽሐፈ የጥበብ መጽሐፍ ከሆኑት አንዱ ሲሆን በርካታ ቁምነገሮችን የያዘ ዘርፈ ብዙ መጽሐፍ ነው:: ለክርስትና ሕይወት እጅግ ጠቃሚ ሆኖ ስለተገኘ ለአንባቢያን እንደማንኛውም የ 66ቱ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ በድረገጽ እንዲገኝ ከአስር በላይ የሆኑ መልካም አድራጊዎች ተሳትፈውበት በዚህ ብሎግ ላይ ወጥቷል:: 

ይህ መጽሐፍ በዋናነት የተገለበጠው ከ 1980 እና 2002 እትም ነው:: እርማቱ የተሰራ ሲሆን ቀጣይ የማሻሻል ስራ ስለሚካሔድበት አንባቢዎች ይህንን በመገንዘብ ለግዜው እያረሙ እንዲያነቡ እንጠይቃለን:: 

በስራው ላይ የተሳተፉ ሰዎች ስም ዝርዝር 
1. ገብረ እግዚያብሔር ኪደ
2. ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
3. ሽንቁጥ አየለ
4. ማቴዎስ ገብሩ
5. ኤልያስ ቀናው
6. በድሉ አበበ
7. አምሳል አያሌው
8. አትናቴዎስ አሸናፊ
9. ስንታየው ጌታቸው
10. አሜክስ አያሌው 
11. ፍጹም ዘሚካኤል 
12. ተአምረ ፅዮን

ለመልካም ትብብራችሁ እግዚያብሔር ዋጋችሁን በሰማይ ይክፈላችሁ::