የኦንያ ልጅ
ስምዖን
፩ የኦንያ ልጅ
ታላቁ ካህን ስምዖንም በሕይወቱ ቤተ መቅደስን እደሰ በዘመኑም ቤተ መቅደስን አጸና::
፪ እንዲሁም የቅጥሩን መሰረትም እጥፍ አድርጎ ሠራ ካህን የሚለብደሰን ነጭ
ልብስ ሰራ
፫ በዘመኑም
የውሀዋች ምንጮች አልጎደሉም የጉድጓዱም ውኋ ብዛቱ እንደ ባሕር ውኋ ነበር
፬ ሕዝቡም
እንዳይወድቁ ይጠነቀቅላቸው ነበር ከተማዋንም ከጠላት ለመከላከል መሸገ ::
፭ ከቤተ
መቅደስ መጋረጃ በወጣ ጊዜም በሕዝቡ መካከል ተከበረ
፮ በደመና
ውስጥ እንደ አጥቢያ ኮከብና በምለዕት ቀን እንደ ሙሉ ጨረቃ ነበር
፯ በልዑል
መቅደስም ላይ እንደምታበራ ፀሀይ ነበረ በብሩህ ደመናም ውስጥ ብርሃንእንደሚስጥ ቀስተ ደመና ነበር
፰ እንደ መጻው
ወራት ጽጌረዳም ነበር በውኋ መፍሰሻ አጠገብ እንደሚያፈራ አበባም ነበር በመከርም ወራት እንደ ሊባኖስ ዛፍ ቅርንጫፍ ነበር
፱ በጥና እሳት ላይ እንዳለ ነጭ ዕጣንም ነበር ተመትቶ እንደርተሰራ
የወርቅ እቃም ነበር በጌትጥ ላይ እንዳለ የከበረ እንቁም ነበር
፲ ፍሬዋ
ብዙእንደሆነ የዘይት እንጨት ከደመና በታች እንደሚያድግ የዋንዛ ዛፍ ነበር
፲፩ እርሱም የክብር ልብሱን በለብስ ጊዜ የመመኪያውንም ጌጥ በለበሰ ጊዜ
ወደ ተቀደሰው መሰዊያ በወጣ ጊዜበቅድስና ልብሱ ተከበረ
፲፪ ከካህናቱም እጅ ከመሥዋዕቱም ሥጋ ክፍል በተቀበለ ጊዜ በመሠዊያው
አጠገብ ይቆም ነበር ወንድሞቹም በዙርያው ቆመው ይጋርዱት ነበር እንደ ሊባኖስ ለጋ ዝግባና እንደ ዘንባባም ዛፍ ይከቡት ነበር
፲፫ እንዲሁም
የአሮን ልጆች ሁሉ የክብር ልብሳቸውን ለብሰው የእግዚአብሔርን መባእ በእጃቸው ይዘው በእስራኤል ማህበር ሁሉ ፊት ይቆሙ ነበር
፲፬ በመሠዊያውም ሥራቸውን ይፈጽሙ ነበር ሁሉን የሚችል የሉዑልንም
መሥዋዕት ያዘጋጁ ነበር
፲፭ የወይኑን ጽዋ ይዞ እጁን አነሣ የወይኑን ዘለላ ደምም አፈሰሰ ለንጉስ
ነገስት ለሉዑል በጎ መዓዛ አድርጎ በመሠዊያው እግር ሥር ያፈስሰው ነበር
፲፮ የአሮን ልጆችም እየጮሁ ምስጋናውን ይናገሩ ነበር ተመትቶ የተሠራ
የብር መለከትም ይነፉ ነበር በልዑልም ፊት ማሳሰቢያሊሆንቃላቸውን ያሰሙ ነበር
፲፯ ያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ያርፉ ነበር ሁሉንበምድር ላይ
በግንባራቸው ይሰግዱ ነበር ሁሉን ለሚገዛ ለሉዑል እግዚአብሔርም ምስጋና ያቀርቡ ነበር
፲፰ መዘምራኑም
በቃላቸው ያመሰግኑ ነበር የዜማቸው ድምጽ ቤቱን ያስተጋባው ነበረ
፲፱ ህዝቡም ወደ ሉዑል እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር በእግዚአብሔር ሕግ
ጸንተው ስራቱን እስኪጨርሱ ድረስ ይቅር በሚል በእግዚአብሔር ፊት ይለምኑ ነበር
፳ ከዚህም በኋላ እርሱ ወራዶ እግዚአብሔርን በረከት በአንደበቱ ይሰጣቸው
ዘንድ በስሙም ይመኩ ዘንድ በእስራኤል ልጆች ማህበር ልይ እጁን አነሣ
፳፩ የሉዑልንም
በረከት ይቀበሉ ዘንድ ዳግመኛ ሰገዱ
፳፪ አሁንም
በሁሉም ቦታ ብዙ ታአምራትን የሚያደርገውን ከእናታችን ማህጸን ጅምሮ ዘመናችንንም የሚያረዝመውን እንደቸርነቱ ይቅርታ
የሚያደርግልንን የሁሉን ፈጣሪ አመስግኑ
፳፫ የልቡና ደስታንም ይሰጠናል በዘመናችንም ሰላምን ያደርጋል ለእስራኤልም
ለዘለአለም
፳፬ በቸርነቱም ከእኛ ጋር የታመነ ነው በዘመናችንም አዳነን
፳፭ ሰውንውቴ
ሁለት ወገኖችን ጠላች ሦስተኛው ግን ሕዝብ አይደለም
፳፮ እነዚህም በሰማርያና በፍልስጤም ተራራ የሚኖሩ በስቂማ የሚኖሩ
የአሞሬዋንም ሰዎች ናቸው ጥበብን ከልብ ያነቃል
የኢየሩሳሌም ሰው የሲራህ አላዛር ልጅ እኔ ኢያሱ ተጥበብና የምክርን ትምህርት በዚህ መጽሐፍ ፃፍኩ
የኢየሩሳሌም ሰው የሲራህ አላዛር ልጅ እኔ ኢያሱ ተጥበብና የምክርን ትምህርት በዚህ መጽሐፍ ፃፍኩ
፳፰ ይህን እንደዚህ የሚያደርግ ከዚያም የሚራቀቅ ብጹዕ ነው ይህንን በልቡ
የሚጠብቅ ጠቢብ ይሆናል
፳፱ ይህን ይሚይደርግ ሁሉን ይችላል የእግዚአብሔርም ብርሃን ይመራዋል