ንጉሡ እዮስያስ
፩ የእዮስያስ
መታስቢያ በቀማሚት ብልሃት እንደተቀመመ ሽቶ ነው እንደ ማርም በአፍ ሁሉ ጣፋጭ ነው በመጠጥም ግብዣ ጊዜ እንደ ዘፈን ነው ::
፪ እርሱ የቀና
ነው ሕዝቡንም መለሳቸው የኃጢአትንም ርኩሰት ሁሉ አስወገደ ::
፫ ልቡናውንም
ወደ እግዚያብሔር አቀና በኃጣንም ዘመን ጽድቅን አጻናት::
፬ ከዳዊት ከሕዝቅያስና ከኢዮስያስ በቀር ሁሉም በድለዋል
፭ የልዑልን ሕግ ትተዋልና ክብራቸውንም ለሌላ ሕዝብ ስጥተዋልና
ነቢዩ ኤርምያስ
፮ የተመረጠችውና የተቀደሰችውን ከተማ አቃጠሏት:: መከራ አጽንተውባታልና
እንደ ነቢዩ ኤርምያስ ትንቢት ጎዳናዋን አጠፉ::
፯ አሠቅይተውታልና እርሱ ግን ነቢይ ይሆን ዘንድ ይነቅል ዘንድ ያጥፍም
ዘንድ እንዲሁም ይተክል ዘንድ ይሠራም ዘንድ በእናቱ ማህጸን ተመረጠ
ነቢዩ ሕዝቅኤል
፰ ሕዝቅኤልንም
የጌትነኑ ራእይ አየ እግዚያብሔርንም በኪሩቤል ሠረገላ ላይ አየው
፱ ጠላቶቹንም በመዓት አሰባቸው የጻድቃንንም ጎዳናቸውን በመልካም አቀና
::
፲ የአስራ
ሁለቱ ነቢያትም አጽሞቻቸው በቦታቸው ለመለሙ ያዕቆብን አጽናንተውታልና በታመነ ተስፋ አድነውታልና ::
፲፩ ዘሩባቤልን
እናገንነው ይሆን እርሱስ በቀኝ እንዳለ እንደ ሐቲም ቀለበት ነው ::
፲፪ የዮሴዴቅ ልጅ ዮሴፅም እንዲሁ ነበር ለዘመናቸውም ቤተ መቅደስ ሰሩ
ለዘላለም ክብር ለተዘጋጀ የእግዚያብሔርንም ሕዝብ አከበሩ
፲፫ የነህምያም መታሰቢያ ብዙ ነው የወደቀች ቅጽር አነሳልን ደጃፎችንም
አቆመልን ቁልፉንም ሠራልን ቤታችንንም ገነባልን ::
፲፬ እንደ ሔኖክ ያለ ሰው በምድር የተገጠረ የለም እርሱ ከዚህ አለም
ተወሰደ
፲፭ እንደ
ዮሴፍ ያለ ሰው አልተወለደም ለወንድሞቹ አለቃ ሆነ ለህዝቡም ኅይል ሆነ ለአጽሞቹም ይቅርይታ አገኝ
፲፮ ሴምና ሴት ከሰው ይልቅ ከበሩ አዳምም ከፈጠረው ሕያው ፍጥረት ሁሉ
ከበረ