፩፤ ልጄ ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ወደ ገዳም ብትሄድ ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ።
፪፤ ልብህን በምግባር አቅና መከራውንም ታገሥ አትጠራጠር ፤በመከራውም ብትጨነቅ አትጠራጠር።
፫፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን ተከተለው ኋላ በፍጻሜ ዘመንህ ክብርህ ትበዛ ዘንድ አትተወው።
፬፤፭፤ የደረሰብህን መከራ ሁሉ በትዕግስት ተቀበል።ወርቅን በእሳት እንዲፈትኑት ጻድቅንም ሰው ችግር በሚያመጣ መከራ ይፈትኑታልና ገንዘብ በተቸገርክበት ወራት መከራውን ታገሥ።
፮፤ እግዚአብሔርን እመነው እንጂ ይረዳሃል ፤ሥራህን አቅና በሱም እመን።
፯፤ እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሰዎች ቸርነቱን ደጅ ጥኗት በመከራ እንዳትወድቁ ከሱ አትራቅ።
፱፤ እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሰዎች በጎ ረድኤቱን ተስፋ አድርጓት ዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር ደስ የሚያሰኝ ቸርነቱን ተስፋ አድርጉ።
፲፤ በዘመን የቀደሙ ሰዎችን አስተውሎ በእግዚአብሔር አምኖ ያፈረ ማነው።እወቁ እሱን በመፍራት መከራውን የታገሰ በመከራ እንደ ጣለው የቀረ ማነውለምኖትስ ቸል ያለው ማነው።
፲፩፤ እግዚአብሔር ይውር ባይ ነውና ርኁሩኅ ነውና ኃጢአትን ይቅርይላል ከመከራውም ቀን ያድናል።
፲፪፤ ለሚጠራጠር ልቡና ወዮለት ለክፉዎች ሰዎች ወዮላቸው ሥራው ሁለት ለሆነ ኃጢአቱን አብዝቶ ለሚሰራ ለኃጢአተኛ ሰው ወዮለት።
፲፫፤ ለሚጠራጠር ሰው ወዮለት አላመነምና፤ ስለዚህ ነገር ከመከራው አያመልጥም።
፲፬፤ ዋጋቸውን ላጡ ሰዎች ወዮላቸው እግዚአብሔር በመዓቱ በተመላባቸው ጊዜ ምን ያደርጉ ይሆን።
፲፭፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይረሱም የሚወዱትም ሰዎች አምልኮቱን ዘጠኙን ሕግጋት ይጠብቃሉ።
፲፮፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ፈቃዱን ይፈጽማሉ የሚወዱትም ሰዎች ሕጉን ይጠበቃሉ።
፲፯፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ልቡናቸውን ለመከራ ያዘጋጃሉ።ሰውነታቸውንም መከራውን ያስቧታል ቸርነቱ እንደ ገናንነቱ ብዛት መጠን ነውና።
፲፰፤ በሰው እጅ ከመውደቅ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻላልና ብለው ሰውነታቸውን በፊቱ መከራውን ያስችሏታል።