፩፤
ለእግዚአብሔር ብሎ መከራውን ለሚታገስ ሰው ጠላቱን ተበቅሎ ያጠፋታል ኃጢያቱንም ያስተሰርይለታል፡፡
፪፤ ባልንጀራህን የምትነቅፈው ኃጢያቱን ይቅር በለው የዚያን ጊዜ ከተለማመጥህ ኃጢያት ህን ያሰሰርይልሃል፡፡
፪፤ ባልንጀራህን የምትነቅፈው ኃጢያቱን ይቅር በለው የዚያን ጊዜ ከተለማመጥህ ኃጢያት ህን ያሰሰርይልሃል፡፡
፫፤ አንተ ሰው
ሆነህ እንዳንተ ያለውን ሰው ሳትቀየም እግዚያብሔርን እንዴት ይቅር በለኝ ትለዋለህ፡፡
፬፤ እንዳንተ
ያለ ሰው ይቅር ሳትል ኃጢአት ህን ያስተሰርይልህ ዘንድ እንግዲህ እንዴት ትለምነዋለህ ፡፡
፭፤ ኃጢአት ህን
አስበህ ጠብን ተዋት፡፡
፮፤ ሞትን
አስበው ፡ መቃብርንም አስበው ትእዛዙንም ጠብቅ፡፡
፯፤ ሕጉን አስበህ ባልንጀራህን አትቀየም ፡ የእግዚአብሔርን ፍርዱን አስበህ
ቁጣውንም አርቃት
፰፤ ቁጣን ክርክርን ተዋት ኃጢአቶች ህንታስነሳቸዋለች ቁጡ ሰው ክርክርን
ያነሳሳዋል፡፡
፱፤ ሐጢያተኛ
ሰው ባልንጀራውን ያደክማል በወዳጆቹም መካከል ነገር ሰርቶ ያጣላል
፲፤ በእንጨቱ ልክ የእሳቱ ነዲዱ ይበዛል በክርክሩም ብዛት ልክ ጠቡን
ያበዛል የሰውም ኃይሉ በቁመቱ ልክ ነው በባለጸግነቱ ብዛት ልክ ቁጣውን ያበዛል፡፡
፲፩፤ መታበይን
የሚያበዛት ሰው ኃጢአትን ይሰራታል ለጠብ የሚቸኩል ሰው ፈጥኖ ደምን ያፈሳል፡፡
ክፉ ምላስ
፲፪፤ ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጥፋለች ሁለቱም ሁለቱም ሁሉ ከ አንድ አፍ ይወጣሉ፡፡
፲፫፤ ብዙ
ወዳጆችን አጣልቷልና ፡ አሚተኛ ለ አንዱ አነትን ለ አንዱ አሰትን የሚናገርን ሰው ይረግሙታል፡፡
፲፬፤ ነገረ
ሰሪ አንደበት ብዙ ሰዎችን አወካቸው ከ አንዱ ወገንም ወደ አንዱ ወገን እንዲሰደዱ አደረጋቸው ብዙ አምባዎችንም አፈረሰች
የመኳንንቱንም ቤት አፈረሰች፡፡
፲፭፡ ቀባጣሪ
አንደበት ሴቶችን ከባሎቻቸው ቤት አስወጥታ ሰደደቻቸው ገንዘባቸውንም አጠፋችባቸው ፡፡
፲፮፤ ነገረ
ሰሪ አንደበት ያልተጠበቀ ሰው ግን ለዘለዓለሙ ከመከራው አያርፍም በፍቅርም አይኖርም ፡፡
፲፯፤ የግርፋት ቁስል መግል ይይዛል የነገረ ሰሪ አንደበት ቁስል ግን
አጥንትን ይሰብራል፡፡
፲፰፤ በጦር ተደብድበው የወደቁ ሰዎች ብዙ ናቸው ነገር ግን በነገሪ ሰሪ
አንደበት እንደጠፉ አይደለም፡፡
፲፱፤ ከሷ የዳነ በጥፋቷም ያልተሰነካከለ በስራቷም ያልጸና በግር ብረቷም
ያልታሰረ የተደነቀ ነው፡፡
፳፤ ሥራቷንም የጸና
ሥራት ነው የምታመጣው መከራ ጽኑ ነው፡፡
፳፩፤ ሞቷም
ጽኑ ሞት ነው ከሷ ሲኦል ትቀላለች፡፡
፳፪፤ በደጋጎች ሰዎች አትደርስባቸውም በእሳት መቃጠልም አያገኛቸውም
፳፫፤
እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎች በሷ ይጠፋሉ በማይጠፋ እሳቷም ታቃጥላቸዋለች፡፡ እንደ አንበሳም ትወረወርባቸዋለች እንደ ነብርም
ትይዛቸዋለች፡፡
፳፬፤ ገንዘብህን በእሶህ ብታጥር ብርና ወርቕንም ብትቆልፍ፡፡
፳፭ ነገርን
መጥነህ ብትናገር በ አንደበት ህም አርምሞን ብታኖር ባማረ በተገባ ነበር፡፡
፳፮፤ ዳግመኛም
በ አንደበት ህ እንዳት ሰናከል በሚያድንህ ጠላት ህም ፊት እንዳትጥልህ ተጠበቅ፡፡