ስለ ማበደርና መበደር
፩፤ምጽዋትን
የሚመጸውት ሰው ለእግዚአብሔር በማደሩ ነው በእጁም የሚበቃ ገንዘብ ያለው ፈቃዱን ያደርጋል፡፡
፪፡በተድላው
በደስታው ጊዜ ከሱ ጋር ደስ ይልህ ዘንድ በተቸገረ ጊዜ ለባልንጀራህ አበድረው፡፡
፫፤ወዳጅህን ጠብቅ ከእሱም ጋር ተማመን በወደድሃትም ጊዜ ጽድቅን
ታገኛታለህ
፬፡ የብድርን
ገንዘብ በመሬት ላይ ወድቆ ያገኙ የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ ናቸው ያበደሩዋቸውን በመከራቸውም ጊዜ የረዷቸውን ባለጸጎች
አደከሟቸው፡፡
፭፤
እስኪበደርህም ድረስ እራስ ህን ይስምሃል ቃሉንም ያደክማል ገንዘብንም እስኪወስድ ድረስ ያባብልሃል በተከፈልከው ጊዜ ግን
ቀጠሮህን ያረዝምብሃል በገንዘብህም ጠብና ክርክርን ይከፍልሃል፡ ያደክምሃል ቀጠሮህንም ያራዝማል፡፡
፮፤
እኩሌታውንም ቢከፍልህ በጭንቅ ነው ዳግመኛም እሱን በምድር ላይ ወድቆ ያገኘኸው ይመስልሃል ይህስ ካልሆነ ገንዘብህን ሁሉ
ታጣለህ ዳግመኛም ጠላት ይሆንሃል ስድቡን ይሰድብሃል እርግማንም ይረግምሃል ሲያከብርህም ያዋርድሃል
፯፤ገንዘባቸውን
እንዳያጡ ከሰውም እንዳይጣሉ በመፍራትና ጠብን ባለመውደድ ገንዘባቸውን የማያበድሩ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡
ስለ ምጽዋት
፰፤ድሃውን ግን
ታገሰው ምጽዋቱንም ስጠው አልፈኸው አትሂድ፡፡
፱፤የምጽዋትን
ነገር የሚናገር አንቀጽ ይህ ነው ችጋረኛ ነውና ድሃውን በምጽዋት ተቀበለው ባዶውንም አትመልሰው፡፡
፲፤ባልንጀራህንና
ወዳጅህን ክታጣ ወርቅህ ተቀብሮ ኪዝግ በድንጋይም ሥር ተቀብሮ ቢጠፋ፡፡
፲፩፤እግዚአብሔር መጽውት ብሎ ስላዘዘህ ወርቅህን ከተቀበረበት አውጥተህ
መጽውት ከወርቅ ድልብ ይልቅ ፈጽሞ ምጽዋት ይጠቅምሃል፡፡
፲፪፤ ምጽዋትን በድሆች ቤት አድልባት እሷ ትሻላለች ከመከራህም ሁሉ
አንተን ማዳን ትችላለች፡፡
ስለ ዋስትና
፲፫፤ በጦር
ቢሆን በመሳሪያም ቢሆን እሷ ቀድማ ጥንተ ጠላት ህን ድል ትነሳልሃለች የለት ጠላት ህንም ታጠፋልሃለች፡፡
፲፬፤ ደግ ሰው
ወዳጁን ይዋሰዋል የማያፍር ሰው ግን ባልንጀራውን ቸል ይላል፡፡
፲፭፤ ስላንተ
ፋንታ ሰውነቱን አሳልፎ ሰጥቷልና የተዋሰህን ሰው ዋጋውን አትንካበት፡፡
፲፮፤ ጠብን ለማጥፋት መዋስ ደግ ነገር ነው፡፡
፲፯፤ኃጢአተኛ ሰው ግን ያዳነውን ሰው ዋጋ ይዘነጋል፡፡
፲፰፤ መዋስ
ብዙ ሰዎችን አሳዘነ እንደ ማዕበልም አወካቸው አርበኞች ሰዎችንም አሳታቸው ልዩ ወደሆኖ አህዛብም አገር እንዲሰደዱ
አደረጋቸው፡፡
፲፱፤ ኃጢአተኛ
ሰው በመዋስ ይጠፋል ለትርፍም የሚሳሳ ሰው በመከራ ይወድቃል፡፡
፳፤የተቻለህን
ያህል ባልንጀራህን ተቀበል ነገር ግን እንዳያስትህ እራስ ህን ጠብቅ
፳፩፤ የኑሮህ
መጀመሪያ የምትበላው እህል የምትጠጣው ውሃ የምትለብሰው ልብስ ነው ቤትህን ግን እፍረ ህን የምት ሰውርበት ነው፡፡
፳፪፤ በሌላ ሰው ገንዘብ ለባእድ ቤት ስት ዘጋጅ ደስ ሲልህ በቤትህ ምሰሶ
ስር ብትቸገር ይሻልሃል፡፡
፳፫፤ለታናሹም
ለታላቁም በጎ ስራን ሥራ በጎ ነገርንም ተናገር፡፡
፳፬፤
ለመቀላወጥ ካንዱ ቤት ወዳንዱ ቤት የሚሄድ ሰው አነዋወሩ ክፉ ነው ባደርህበትም ቦታ ክፉ ነገር እንዳትናገር እወቅ፡፡
፳፭፤ ይኸስ
ካልሆነ ትበላለህ ትጠጣለህ ምስጋና የለህም ከዚህ ሁሉ ጋራ ክፉ ነገር ይመልሱልሃል፡፡
፳፮፤ በገንዘብ በተዘጋጀ ህ ጊዜ ግን አማቻችን ገብተህ ማዕድን ሥራ
ያለህንም አብላን ይሉሃል።
፳፯፤ ብትቸገር ግን ቤተሰባችን ውጣ አማቻችን ደረሰ ቤታችንን እንወዳለን
ይሉሃል፡፡
፳፰፤ ይህ ነገር ባዋቂ ሰው ዘንድ ጭንቅ ነው ያሳደርከው ሰው ያዋርድሃል
ያበደርከውም ሰው ይሰድብሃል፡