፩፤ በግብዝነት
ሐጢያትን የሚሰሩዋት ብዙ ሰዎች ናቸው ገንዘቡ ይበዛ ዘንድ የሚወድ ሰው ፊቱን ወደ ፍቅረ ንዋይ ይመልሳል፡፡
፪፤ በቅጥር መካከል ድንኳን ይተከላሉ በንግና በዋጋ መካከል ኃጢያት
ትመጣለች፡፡
፫፤ እግዚአብሔርን ፈርቶ ካልተጠበቀ የቤቱ ጥፋት አይዘገይም፡፡
የሕይወት መመዘኛ
፬፤ በወንጠፍት መካከል አሰር ይከማቻል እንደዚሁም ሁሉ ሰውን ኃጢያት ታገኘዋለች፡፡
፭፤ የሸክላ
ዕቃን እሳት ይፈትነዋል ሰውንም የልቡናው አሳብ ይፈትነዋል ፡፡
፮፤ ተክል
የሚጠብቅ ሰው ፍሬውን ያያል እንደዚሁም የሰው ነገሩ የልቡናውን ፍቃድ ይገልጥበታል፡፡
፯፤ ሰውን
ከስራው የተነሳ ይፈትኑታልና ሰውን ሳትጠይቅ አታድንቀው፡፡
፰፤ጽድቅን
ብትተክላት ታገኛታለህ እንደከበረ መሉጣ ግምጃም ትለብሳታለህ፡፡
፱፤ ወፍ ከዘመዱ ጋራ ይኖራል ጽድቅም በሚሰሯት ሰዎች ዘንድ ትኖራለች
፲፤ አንበሳ
የሚበላውን ያድናል ኃጢያትም የሚሰሩዋትን ሰዎች ታድናለች፡፡
፲፩፤ እውነተኛ
ሰው ሁል ጊዜ ጥበብን ያስተምራል የሰነፍ ሰው ግን እውቀቱ እየነጋ እንደጨረቃ ይከፈልበታል
፲፪፤ በሰነፎች ዘንድ ጊዜውን ተጠበቅ በብልሆች ሰዎች ዘንድ ግን ሁልጊዜ
ነገሩን ተረዳ፡፡
፲፫፤ የሰነፎች ነገር ያበሳጫል ሳቃቸውም የኃጢያት ተድላ ደስታ ነው፡፡
፲፬፤ ብዙ መሐላን የሚምል ሰው ራስ ስቅጥጥ ስቅጥጥ ያደርጋል፡፡
የትዕቢተኛ ሰው ክርክርም ዦሮ ያደነቁራል፡፡
፲፭፤
የትዕቢተኞች ክርክራቸው ደም ያስፈሻል ክርክራቸውም ለሚሰማቸው ሰው ድካም ነው፡፡
፲፮ ፤
የባልንጀራውን ሚስጢር ያወጣ ሰው መታመኑን አጠፋ ከዚህም በኋላ ወዳጅ አያገኝም፡፡
፲፯፤ ወዳጅህን
ጠብቅ ከእርሱም ጋር ተማመን ሚስጢሩን ብታወጣበት ግን እንግዲህ ፈጽመህ በኋላው አትከተለውም፡፡
፲፰፤ ሰው ጠላቱን እንዳጠፋ የወዳጅህን ወንድሜ ፡ ወንድሜ ማለትን አጠፋህ
፡፡
፲፱፤ ወፍ ከእጅህ እንድታመልጥ ወዳጅህ እንደዚሁ ከአንተ አመለጠህ ፡፡
፳፤ ሚዳቋ ከወጥመድ እንድታመልጥ ፈጽሞ አምልጦሃልና ከዚህ በኋላ
አትከተለውም
፳፩፤ ቁስል
ቢሆን ተኩሰው ባዳኑት ነበር የተሳደበም ሰው ባካካሱት ነበር የባልንጀራውን ሚስጢር ያወጣውን ሰው ግን ተስፋ ይቆርጡለታል፡፡
ስለ ግብዝነት
፳፪፤ክፋቱን ማስተው የሚችል የለምና ባይኑ የሚጠቅስ ሰው ልቡናው ያማረ
አይሆንም ፡፡
፳፫፤ ለዓይንህ
ግን ከንፈሩን ይመጥልሃል በተናገርኸው ሁሉ ያመሰግንሃል ኋላ ግን በቃሉ ይወነጅልሃል በተናገርኸው ቃል ያስጣል፡፡
፳፬፤
የጠላኻቸው ሰዎች ብዙ ናቸው ነገር ግን እንደሱ አይደሉም ፡እግዚአብሔርም እሱን ጠላ፡፡
፳፭፤
በባልንጀራው ድንጋይ የሚወረውር ሰው በራሱ ላይ ትወርዳለች፡ የበደል ግርፋት ግን ቁስል ይታወቃል፡፡
፳፮፤
በባልንጀራው ጉድጓድ የቆፈረ ሰው እሱ በውስጡ ይወድቃል ወጥመድም ያዘጋጀ ሰው በወጥመዱ ይያዛል፡፡
፳፯፤ኃጢያት
የምትመጣበትን አያውቅም፡፡
፳፰፤ የትዕቢተኞች ስድባቸው ፡ ሳቃቸው እንደ አንበሳ ታድናቸዋለች ተበቅላ
ታጠፋቸዋለች፡፡
፳፱፤ በደግ
ሰው ጥፋት ደስ የሚላቸው ሰዎች በፍዳ ይያዛሉ የሚሞቱበት ጊዜ ሳይደርስ መቅሰፍት ያጠፋቸዋል፡፡
፴፤ ቁጣና መዓትም የሚያስጸይፉ ናቸው ሐጢያተኛ ሰውም ዘንድ ጸንተው
ይኖራሉ፡፡