፩፤
እግዚአብሔር፥ አዳምን ከምድር ፈጠረው፤ ዳግመኛም ወደ ምድር ይመልሰዋል።
፪፤ ዘመንን፣ ቀንን፣ በቊጥር ሰጣቸው፤ በውስጧም ያለውን ፍጥረት ሁሉ
አስገዛቸው።
፫፤ እየራሳቸው ኃይልን አሳደረባቸው፤ በምሳሌውም ፈጠራቸው።
፬፤ ፍጥረቱ ሁሉ፦ ይፈሩዋቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩዋቸው አደረገ።
፭፤ ከብቶችንና አውሬዎችን፣ ወፎችንም፤ ይገዟቸው ዘንድ እንዲገዟቸው
አደረገ።
፮፤ አንደበትንና ቃልን፣ ዦሮንንና ዓይንን፣ በሚያስቡ ገንዘብ ልቦናንም
ሰጣቸው።
፯፤ ጥበብን፥
ማወቅንም አጠገባቸው፤ ክፉንና በጎንም አሳያቸው።
፰፤ የሥራውን ገናንነት፥ መፈራቱንም ያሳያቸው ዘንድ፤ በልቦናቸው ፍርሃትን
አሳደረባቸው።
፱፤ የከበረ ስሙን ያመሰግኑት ዘንድ።
፲፩፤ ጥበብን ሰጣቸው፥ የሚያድናቸው ሕጉንም አወረሳቸው።
፲፪፤ ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር፥ መሐላንም ተማማላቸው፤ ፍርዱንም
ነገራቸው።
፲፫፤
የጌትነቱንም ገናንነት ዓይኖቻቸው አዩ።
፲፬፤ ከኃጢአቱ
ሁሉ፥ ተጠበቁ አላቸው።
፲፭፤
የጌትነቱንም ቃል፥ ዦሮቻቸው ሰሙ፤ ሁሉንም፥ ባልንጀራችሁን ውደዱ ብሎ አዘዛቸው።
፲፮፤ ሥራቸውም፥ ሁለጊዜ በፊቱ ነው፤ ካይኖቹም የሚሠወሩበት የላቸውም።
፲፯፤ ለአሕዛብ ሁሉ፥ ነገሥታቱን አነገሠላቸው።
፲፰፤ እስራኤል
ግን፥ የእግዚአብሔር እድል ሆነ።
፲፱፤ ሥራቸውም
ሁሉ፥ በፊቱ እንደ ፀሐይ ነው፤ ዓይኖቹም፥ ሁለጊዜ ሥራቸውን ያያሉ።
፳፤
ኃጢአታቸውም፥ ከሱ አልተሠወረችም፤ በደላቸውም ሁሉ፥ በእግዚአብሔር ፊት የተገለጠ ነው።
፳፩፤ የሰው ምጽዋቱ፥ ከሱ ጋራ እንደ ማኅተም ነው።
፳፪፤ የሰው
ዋጋው፥ እንደ ዓይን ብለኔ ትጠበቅለታለች።
፳፫፤ ኋላ
ተመልሶ፥ ዋጋቸውን ይሰጣቸዋል፤ የኃጢአታቸውንም ፍዳ፥ ወደ ራሳቸው ይመለሳል።
፳፬፤ ነገር
ግን፥ ንስሐ የሚገቡትን ምክንያት ሰጣቸው፤ ተስፋቸውን ያጡ ሰዎችንም፥ ደስ አሰኛቸው።
የንሰሐ ጥሪ
፳፭፤ በንስሐ፥
ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፤ ኃጢአትንም ተዋት፥ ከኃጢአትህ ተመልሰህ፣ በፊቱ ተለማመጥ።
፳፮፤ ፈጽመህ ከኃጢአትህ፥ በንስሐ፣ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፤ ኃጢአትን
ሁሉ ጥላ፥ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ፈጽም።
፳፯፤ በሕይወት ሳሉ፥ እንደሚገዙለት ሰዎች፤ እግዚአብሔርን፥ በመቃብር
የሚያመሰግነው ማነው።
፳፰፤ የሞተ
ሰውን ግን፥ ንስሐ እንደ ኢምንት አለፈው፤ በሕይወት ሳለህ፥ ደስ እያለህ፤ እግዚአብሔርን አመስግነው።
፳፱፤ የእግዚአብሔር፥ ቸርነቱ ብዙ ነው ነውና የሚገዙለትን ሰዎች ይቅር
ይላቸዋል።
፴፤ ሰው፥ ሟች
ስለ ሆነ፤ ሰው ሁሉ፥ በሕይወት ጸንቶ መኖርን አይችልምና ይቅር ይላቸዋል።
፴፩፤ ከፀሐይ፥ የሚነጻ ምን አለ፤ እሱስ ስንኳ ያልፋል። እንዲህ መሆን
ሳለ፥ ደማዊና ሥጋዊ፤ ክፉ ነገርን ያስባል።
፴፪፤ እሱ
ግን፥ የሰማይን ምጥቀት ያውቃል፤ ሰው ሁሉ ግን፥ አመድ፣ ትቢያ፤ ነው።