Sunday, October 6, 2013

ምዕራፍ ፵፫




. ጠፈርን በህዋው ላይ አጸናት ሰማይንም ማየት በጸሐይ ብርሃን ነው፡፡

. ብርሃኑን ያሳይ ዘንድ ጸሐይን ያወጣል የሰማይ ብርሃን ሥራትም ድንቅ ነው፡፡
 
. በዋዕዩም አገሩን ያቃጥላል ዋዕዩንስ ማን ይቀዋወመዋል፡፡
 
. ዋዕዩም እንደሚነድ እሳት ያቃጥላል የጸሐይ ሦስተኛ ብርሃኗ ተራሮችን ያቃጥላቸዋል፡፡ የእሳት ዋዕይ ከሱ ይገኛል ብርሃኑንም ማየት አይን ያጣምማል፡፡

. የፈጠረው እግዚአብሔርንም ደግ ነው በቃ ሁሉም ፈጥኖ ይሄዳል፡፡
 
. ጨረቃም ለሰው ሁሉ ምልክት ነው ላገሩም ሁሉ ምልክት ነው በሷም ቀን ይለያል፡፡
 
. በጨረቃም የበዓላቱ ምልክት ይታወቃል ሕጸጽ እያደረገ የሚያልቅ ብርሃን እሱ ነው፡፡
 
. ጨረቃስ እንደስሟ ናት ከከዋክብትም እንድትበልጥ ድንቅ ነው በሰማ ሰራዊት በከዋከብት ሥራትም ሕጸጽና ምላትን እንድታፈራርቅ ድንቅ ነው በሰማይ ሰራዊት በከዋክብትም መካከል ሁና ታበራለች፡፡
 
. የሰማይ ጌጥ የከዋክብት ብርሃን ነው፡፡ እግዚአብሔር በፈጠረው በጠፈር ሁነው ለዚህ ዓለም ያበራሉ፡፡
 
. በጌትነቱ ቃል ጸንተው ይኖራሉ ከሥራታቸውም ወጥተው አያልፉም፡፡
 
፲፩. ብርሃኑ ፈጽሞ ያማረ ነውና ቀስተ ደመናወን አይተህ ፈጣሪውን አመስግነው፡፡
 
፲፪. በሰማይ ይከፈላል ብርሃኑም ይከበዋል የእግዚአብሔርም ቃሉ ይከፍለዋል፡፡

፲፫. በትዛዙም በረድ ይዘንባል መብረቅም በፈቃዱ ፈጥኖ ይወርዳል፡፡
 
፲፬. ስለዚህ ነገር እግዚአብሔር ቦታውን ይገልጣል ደመናትም እንደ ወፎች ይበራሉ፡፡
 
፲፭. በገናንነቱም ደመናትን ያጸናቸዋል የበረድ ድነጋይም ይከፈላል፡፡
 
፲፮. በጎበኛቸውም ጊዜ ተራሮች ይነዋወጣሉ በፈቃዱም የምሥራቅ ነፋስ ይነፍሳል፡፡
 
፲፯. የመብረቁም ቃል ምድርን ያስፈራታል የምዕራብ ነፋስም ሰውነትን ያደርቃታል ጉምንም እነደሚበሩ ወፎች ይበትነዋል አወራረዱም እንደ አንበጣ አወራረድ ነው፡፡
 
፲፰. ያነጣጡም መልክ ለዓይን ድንቅ ነው በረድን እነደ ጨው ይቀላቅላታልና ዝናምነቱም ለልብ ድንቅ ነው፡፡
 
፲፱. ጉምንም በዚህ ዓለም ይበትነዋል ውርጭም ከረጋ በኋላ ሽፎ እንደሆነ እንደ ብርሌ ስባሪ ብልጭ ይላል፡፡
 
. የቀዘቀዘ የምሥራቅ ነፋስም ይነፍሳል ውርጭም በውኃ ላይ ይረጋል በውኃው አዟሪ ላይ ይቆማል እንደ ብረት ልብስም በውኃ ላይ ጸንቶ ይኖራል ውኃይቱንም ይሸፍናታል፡፡
 
፳፩. ተራራውን ይበላል ምድረ በዳውንም ያቃጥላል ሥሩንም እነደ እሳት ያደርቀዋል፡፡
 
፳፪. የሰው ሁሉ ሕይወቱ ዝናም ፈጥኖ ቢዘንም ዝናምም ወደ ምድር በወረደ ጊዜ ደስ ያሰኛል፡፡
 
፳፫. በእግዚአብሔር ምክር ውኃው ይደርቃል ከዚህ በኋላ ኢያሱ ጸሐይን አቆመ፡፡
 
፳፬. በባሕርም የሚሄዱ ሰዎች መከራዋን ይናገራሉ እኛም ሰምተን እናደንቃለን፡፡

፳፭. በዚያም ሥራው ፈጽሞ ድንቅ ነው፡፡ ከብትን መግዛት በየወገኑ ነው፡፡
 
፳፮. በጎ መዓዛ አድርጎ ሊቀበለው ከነሳቸውም መሥዋዕት ይሠዋለታል በቃሉም ሁሉ ይደረጋል፡፡
 
፳፯. ብዙ ነገርን እንናገራለን የነገሩ መጨረሻ እሱ ብቻ ነው እንጂ ነገር ግን መጨረስ አንችልም፡፡
 
፳፰. ከፍጥረት ሁሉ እሱ ይበልጣልና እሱን ማመስገን ምን ያህል እንችላለን፡፡
 
፳፱. እግዚአብሔር ልውጥ ነው የሚያስፈራ ነው ልቁንም ገናንነቱም ያስፈራል ሓይሉም ድንቅ ነው፡፡

. ጨርሳችሁ ማመስገንን አትጠነቀቁምና ምንም ባትጠነቀቁ የተቻላችሁን ያህል እግዚአብሔርን አመስግኑት አግኑት፡፡ ዳግመኛም ከዚህ ሁሉ በልጣል በፍጹምእውቀታችሁም አግኑት አትደርሱበትምና ምንም ባትደርሱበት እሱን ማመ ስገንን ቸል አትበሉ፡፡
 
፴፩. ከቶ የሚነግረን ማነው በገናንነቱስ ልክ ማን ያገነዋል፡፡

፴፪. ማይታየው ከዚህ የሚበልጠው ፍጥረቱ ብዙ ነው ያየነው ፍጥረቱ ግን ጥቂት ብቻ ነው፡፡
 
፴፫. እግዚአብሔር ሁሉን ፈጥሯልና ለደጋጎች ሰዎች ጥበብን ሰጣቸው፡፡