Sunday, October 6, 2013

ምዕራፍ ፵፬



፩፤ የከበሩ ሰዎችን የጥበብና ምስጋና እናመስግናቸው እግዚአብሔር ብዙ ክብር ሰጥቷቸዋልና።
፪፤ ከተወለዱም ጀምሮ አግኗቸዋልና አባቶቻችንንም በዘመናቸው እናመስግናቸው። 
፫፤ በኃይላቸው ስማቸውን ያስጠሩ ሰዎችም በመንግስታቸው ገዙ በጥበባቸው የሚመክሩ ትንቢትንም የሚናገሩ ነቢያት ደጋጎች ናቸው እናመስግናቸው ። 
፬፤ የአህዛብም ነገስታት በሰልፋቸው ደጋጎች ናቸው እናመስግናቸው የህዝቡም ጸሃፊዎች በጥበባቸው በልባቸውም ባለ በቃላቸው ጥበብ ደጋጎች ናቸው እናመስግናቸው ።
፭፤ ምስጋናን ያማረ መሰንቆን የሚፈልጉ በሕዑጻን/?/ እንደ ተጻፈ አድርገው የሚያመሰግኑ ሌዋውያን ደጋጎች ናቸው እናመስግናቸው ።
፮፤ ባለጸጎች የሆኑ ገንዘባቸው የሚበቃቸው በቤታቸው በሕይወት የሚኖሩ ሰዎች ደጋጎች ናቸው እናመስግናቸው ። 
፯፤ እነዚህ ሁሉ በዘመናቸው የከበሩ በሕይወታቸው የተዘጋጁ ናቸው እናመስግናቸው ። 
፰፤ ከነሳቸውም እሱን የሚናገሩት የከበረ ስምንም የተዉ አሉ።
፱፤ የሚያስባቸው የሌለ የጠፉም ተፈጥረውም እንዳልተፈጠሩ የሆኑ ፤ተወልደው ወዳለመወለድ የተመለሱ አሉ ልጆቻቸውም እንደነሳቸው ጠፉ።
፲፤ በልበ ሥላሴ የሌለ የተጻፉ ጽድቃቸው ያልተዘነጋችባቸው። 
፲፩፤ ያማረች ርስታቸውም ከልጆቻቸው ጋራ ለዘለዓለም ጸንታ የምትኖር እነዚህ ሰዎች ግን ደጋጎች ናቸው እናመስግናቸው ። 
፲፪፤ ልጆቻቸውም በሥራቸውጸንተው ይኖራሉ።
፲፫፤ ክብራቸውም አያልቅም። 
፲፬፤ ሥጋቸውም በተድላ በደስታ ተቀበረ ስማቸውም ለዘለዓለም ጸንታ ትኖራለች። 
፲፭፤ አህዛብ በጥበባቸው ይናገራሉ በአህዛብም ሸንጎ የመሰግኗቸዋል።
፲፮፤ ሄኖክ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው እግዚአብሔርም እሱን ከሞት ሰወረው ንሰሐ ይገቡ ዘንድ ንሰሐ ለሚገቡ ሰዎች አብነት ሆነ።
፲፯፤ ኖኅም በውነት ፍጹም ሆኖ ተገኘ በጥፋትም ዘመን እሱ ለሰውምግብ ሆነ የጥፋትም ውኃ በወረደ ጊዜ የታመነ ሆኖ ተገኘ። 
፲፰፤ የጥፋት ውኃ ሰውን ሁሉ እንዳያጠፋው እግዚአብሔር ከሰ ጋራ ለዘለዓለሙመሐላን ተማማለ። 
፲፱፤ የአህዛብም ሁሉ አባት አብርሃም ደግ ነው እናመሰግነውየከበረ ሕጉን የጠበቀ እንደሱ ያለ ሰውም አልተገኘ።
፳፤ እግዚአብሔር በሰውነቱ ከሱጋራ ተማማለ አብርሃምም የእግዚአብሔርን ሕግ ጠበቀ በፈተነውም ጊዜ የታመነ ሆኖ ተገኘ። 
፳፩፤ አህዛብ በልጆቹ ይከብሩ ዘንድ እንደ ባህር አሸዋም ያበዘቸው ዘንድ ልጆቹም እንደ ሰማይ ኮከብ ይበዙ ዘንድ ከባህር እስከ ባህርም ያወርሳቸው ዘንድ ከውቅያኖስም እስከ አድማስ ድረስ ያወርሳቸው ዘንድ ስለዚህ ነገርበ መሐላ ቃልኪዳን አጸናለት።
፳፪፤ ለይስሐቅም ስለ አባቱስለ አብርሃም ደግነት እንደሱ ቃልኪዳንን አጸናለት በረከትም ለሰው ሥራት ሆና ጸናች። 
 
፳፫፤ በያዕቆብ ሰውነት አደረች በረከቱም ተገለጠችለት እሷንም ርስት አድርጎ ሰጠው፤ርስታቸውንም እየወገናቸው ላሥራ ሁለቱ ነገድም ርስታቸውን ከፈላለቸው።
፳፬፤ የከበሩ ሰውም ሁሉዘንድ መወደድን ያገኙ በሰውና በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደዱ ደጋጎች ሰዎችን በነሳቸው አስነሳ።