፩. እሱ
እግዚአብሔር ስለ መረጠው ጌትነቱ እንደ እጁ ሥራ ነውና ባለመድኃኒትን አክብረው፡፡
፪. ሕይወት
ከእግዚአብሔር የሚገኝ ሲሆን ድርጎውን ከንጉሥ ይቀበላል፡፡
፫.
ባለመድኃኒትን በጥበቡ ያከብሩታል፡ በመኳንንትም ዘንድ ይመሰገናል፡፡
፬.
እግዚአብሔር መድኃኒትን ከምድር ፈጥሯልና አዋቂ ሰው ባለመድኃኒትን አይንቀውም፡፡
፭. ታምራቱን
ያውቁ ዘንድ ውሃ በእንጨት የጣፈጠ አይደለምን፡፡
፮. በታምራቱ ይክብሩ ዘንድ እግዚአብሔር ለሰዎች ጥብን ሰጣቸው፡፡
፯. በመድኃኒቱ
ያድናቸዋል በሽታቸውንም ያርቅላቸዋል፡፡
፰. በሚያድኑ
ገንዘብ ከነሳቸው መድኃኒት ያደርጋሉ እሱም ለሀገር ፍቅርን ያጣል፡፡
፱. ወደ
እግዚአብሔር ለምን እንጂ ልጄ በሽታህን ቸል አትል እሱ ከደዌህ ይፈውስሃል፡፡
፲. ኃጢአትነም
ተዋት እደ ልቡናህን አቅና ልቡናህንም ከኃጢአት ለሁሉ አንጸሸ፡፡
፲፩. በመዓህን
አግባ አስበህ ስንዴህን አግባ የተቻለህን ያህል መስዋዕትህን አብዝተህ አቅርብ፡፡
፲፪.እግዚአብሔር
እሱን መርጦታልና ለባለመድኃኒት ሥራውን ሥራት እሱን ትሻዋለህና ካንተ አታርቀው፡፡
Verse ፲፫-፲፬
፲፭. እግዚአብሔር የበደለ ሰው ግን ባለመድኃኒትን አግመኝ ተኩሰኝ ብሎ
በባለመድኒት እጅ ይወድቃል፡፡
፲፮. ልጄ
ለሞተ ሰው አልቅስለት እዘንለት ራስህንም አሳዝን እንደ አግሩም ግዕዝ ተዝካር አውጣለት፡፡ ያገለገለህን ሰው ሞት ቸል
አትበል፡፡
፲፯. ምር ብለህ
አልቅስለት አጽንተህም እዘንለት እንደ እንደ አግሩም ግዕዝ አልቅስለት ስ አግሩም ግዕዝ አንድ ቀን ሁለተ ቀን አልቅስለት፡፤
፲፰. የብስጭት ኃዘን ኃይል የሚያደክም ስለ ሆነ ስለ የብስጭት ኀዘን
እንደይገባህ ከዚህ በኋላ ልቅሶህን ተው፡፤
፲፱. የብስጭት
ኃዘን ትካዝ ለሞት ያደርሳል የድሀ ዘኑ ሁሉ በብስጭት ኃዘን ያልቃል፡፡
፳. የብስዕት
ኃዘን ወደ ልቡናህ አታግባ የብስዕት ኃዘንን ካንተ አርቃት፡፡
፳፩.ድህነት
እንደሌለባት እወቅ ራስሀን ታሳዝናለህ ነገር ግን ጠምትጠቀመው ነገር የለም፤፡፡
፳፪. እኔ የተቀበልሁትን
ዋጋ አስተውል አንተም እንደዚሁ ዋጋ እንድትቀበል እወቅ፡፡ እኔ ዛሬ ብቀበል አንም ገር እንድትቀበል እወቅ፡፡
፳፫. የሞተ
ሰውስ አረፈ ነገር ግን ነፍሱ ታርፍ ዘንድ ተዝካር አውጣት ከዚህ በኋላ ልቅሶህን ተው፡፡
፳፬. የጸሐፊ
ጥበብ በተሸመበት ወራት ይታወቃል ሥራውን የሚያበዛ ሰው አይራቀቅም፡፤
፳፭. ርፉን
የሚያፀና ሰው በምንም በምን አይራቀቅም በርሻው ይታበያል በሬውን ይገርፋል በሥራውም ይመላለሳል ነገሩ ሁሉ አባት ያበላ ዘንድ
ነው ወይፈኑንም
፳፮. እንዲያቀና ድረስ ይደክማል፡፡
፳፯. ሌሊቱ ቀን
የሚሆንባቸው የጠራቢዎች አቀቃና እንጨት ጠራቢን እንደሱ ናቸው የማህን ቅርጽ ጠየሙቀርጹ ከየሚያለዝን ሰዎች እንደሱ ናቸው
አሳቡም ሁሉ በየመልኩ መስ ይሠራ ዘንድ ነው ምክሩ ለሁሉ ማኅተሙን ማለዘብ ይጠነቀቅ ዘነድ ነው፡፡
፳፰. በወናፍ
አጠገብ የሚቀመጥ የብረትም ሥራ የሚማር አንጥረኛ እንደሱ ነው፡፤ የወናፉም ጢስ ሰውነቱን ያሻክረዋል፡፡ እሳቱም ሰውነቱን ንደ
ሰም ያቀልጣል የመዶሸውም ድምጥ ጆሮውን ያደነቁረዋል፡፡ ዓይኖቹም ባለጸጋ የሚሆንበትን ሥራ ይለከታሉ በልቡም ሥራውን ይጨርስ
ዘንድ ያስባል ትጋቱም ባለጸጋ የሚሆንበትን ሥራና ወናፉን ያሳምር ዘንድ ነው፡፡
፳፱. በሥራው
የሚቀመጥ ሸክላ ሠሪም እንደሱ ነው በእግሩም መንኩራኩሩን ያዘራል ሥራውም ጨርስ ዘን ሁልጊዜ ያስባል፡፡ የሥራውንም ሁሉ
ይቁጥራል፡፡
፴. በእጁም
ጭቃውን መስሎ ይሠራል በእንግሩ ጭቃውን ሲረግት ኃሉን ያደክማል የልቡናውም አሳብ ሥራውን ይጨርስ ዘንድ ነው፡፡ ትጋቱም
መወልወያውን ያዞር ዘንድ ነው፡፡
፴፩. እነዚህ
ሁሉ የጃቸውን ሥራ ተስፋ ያደርጋሉ ሁሉ በሥራቸው ይራቀቃሉ፡፡
፴፪. ያለነሳቸውም
ባገር መኖር አይቻልም፡፡
፴፫. ነገር ግን
በሸንጎ ምክርን አያስመክሯቸውም ባደባባይም ከመኳንንት ጋራ አያስቀምጧቸውም የቅጣት ፍርድንም አያስፈርዷቸውም አያስገዟቸውም
አያሰለጥኗቸውም፡፡
፴፬. ያገርን
ፈቃድ ያጸናሉ እንጂ ነገርን መስሎ በመናገር አይኖሩም ጸሎታቸውም በሥራቸውም ይራቀቁ ዘንድ ነው፡፡
፴፭. እውቀት
ግን በልቡ ለሚተጋ ሰው ነው የእግዚአብሔርንም ሕግ ለሚያስብ ሰው ነው፡፡ .