Sunday, October 6, 2013

ምዕራፍ ፵




፩. በሰው ተፈጥሮ ያለ ሞትን መጠራጠር ጽኑ ነው ከናታቸው ሆድ ከተወለዱ ጀምሮ በሁሉ እናት በመቃብር ሆድ እስኪቀረበሩ ድረስ በአዳም ልጆች ላይ የከበደ ሸክም ሞት አለ፡፡ 
፪. የምታስደነግጥ ናት ልብንም የምታስፈራ ናት በመንግሥት ዙፉን ካለ ንጉሥ ጀምሮ ባመድና በትቢጣ ላይ፡፡ 
፫. እስከሚተኛ ድሀ ድረስ ዕለተ ሞትን መጠራጠር በአዳም ልጆች ላይ ሁሉ አለ፡፡ 
፬. ቁጣ ቅናት ገዝንዝ ሰው ማወክ ሞትን መፍራት፡፡ 
፭.ክርክር ሰውን ማማት ይህ ሁሉ በሰው ልቡና አለ ነገር ግን በመኝታው በተኛ ጊዜ የሌሊት እንቅልፍ አሳቡን ይለውጠዋል፡፡ 
፮. ዕረፍቱም እንደ ኢምንት ጥቂት ነው፡፡ ይህ ሁሉ በመኝታው ይታወቃል አንድ ጊዜ እንደ ሸንጎ ተከማችቶ ያገኘዋል የልቡናውን ምክር የሚያወላውላት ሰው በሰልፍ እንደሚሸሽ ሰው ይናገራታል፡፡ 
፰. ይህ ሁሉ እስከ ከብት ድረስ በሰው ላይ አለ ይህም በኃጢአተኞች ሰዎች ላይ ሰባት እጥፍ ይብሳል፡፡ 
፰. ሰልፍ መታበይ ቸንፈር ጦር ቀጠና የልብ ቁስል መቅሠፍት፡፡ 
፱. ይህ ሁሉ በኃጢአተኞች ሰዎች ላይ ኜተጠረ ስለነሳቸውም ኃጢአት የጥፋ ውኃ መጣ፡፤፤
፲. ሁሉ ከምድር ተፈጠረ ሁሉም ወደ ምድር ይመለሳል የወንዙ ውኃ ሁሉ ወደ ውቅያኖስ ይለሳል፡፡ 
፲፩. ሰዎችም ሁሉ ወደ መቃብር ይለሳሉ ከህደት ትጠፋለች ሃይማት ግን ለዘለዓለሙ ትፀናለች፡፡ 
፲፫. ሠርቆ ቀምቶ ያጠራቀሙት ገንዘብ እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈጥኖ ይጠፋል ዝናም በዘመነ ጊዜ መብረቅ ተሰምቶ እንዲጠፋ እንደዚያ ፈጥኖ ይጠፋል፡፡
፲፬. እግዚአብሐየር ሥልጣኑን በገለጠ ጊዜ ደስ ያሰኛል የሚክዱት ሰዎች ግን ፈጽመው ይጣሉ፡፡
፲፭. የኃጢአተኞች ሰዎች ልጆች ልጆቻቸው አይበዙም የኃጢአተኞች ሰዎች አባትነታቸው በሚያድጥ አለት ላይ እንደ ወደቀዘር ነው፡፡ 
፲፮. ዝናም በሁሉ ላይ ይዘንማል በወንዝ ዳር ያለ አኻያ ከፈላ ከቀጤማ ተለይቶ ተነቃቅሎ እንዲወድቅ አባትነታቸው እንዲዚያ ይጠፋል፡፡ 
፲፯. ይግዚአብሔር ስጦታ ግን በበረከት ጊዜ እግዚአብሔር እንደ ፈጠራት እንደ ገነት ነው፡ ምጽዋትም ለዘላለሙ ጸንቶ ይኖራል፡፡ 
፲፰. በገንዘብ የተዘጋጀው ሰው ሕይወቱ የሀበላው የጠጣው ቢስማማው ነው፡ ከነዚህም ከሁለቱ ይልቅ ተቀበረ ወርቅ ማግኘት ደስ ያሰኛል፡፡ 
፲፱. ያገር ሕንፃና ልጆችም ስምን ያስጠራሉ፡ ከነዚህም ከሁለቱ ይልቅ የተቀበረ ወርቅ ማግኘት ደስ ያሰኛል
፳. ዘፈንና ወይን ልቡናን ደስ ያሰኛሉ ከነ ዚህም ከሁለቱ ይልቅ ጥበብን መውደድ ደስ ያሰኛል፡፡
፳፩ በገናና መሰንቆ ሰውነትን ደስ ያሰኛታል ከሁለቱም ይልቅ ልዝብ አንደበት ደስ ያደኛል፡፡ 
፳፪ ደም ግት ከመልክ ጋራ ዓይንን ደስ ያሰኛታል፡፤ ከሁለቱም ይልቅ ቡቃያ ደስ ያሰኛል፡፤ 
፳፫ አማችና ወዳጅ በዘመናቸው ይጠቀውማሉ ከሁለቱ ይልቅ ደግ ሴት በሏን ስት ታሰኘዋለች፡፡ 
፳፬. ረዳትና ወንድሞችም በመከራ ቀን ይጠቅማሉ፡ ከሁለቱም ይልቅ ለማዳን ምጽዋት ትሻላለች፡፡ ፤
፳፭. ብርና ወርቅ አገር ያጸናሉ ከሁለቱ ይልቅ በጎ ምክር ደስ ታሰኛለች፡፡ 
፳፮. ገንዘብና ባለጸግነት ልቡናን ደስ ያሰኛሉ ከሁለቱ ይልቅ እግዚአብሔርን መፍራት ይበልጣል 
፳፯. እግዚአብሔርነ መፍራት የምታሳጣው የለም አጋዥም አትሻ፡፡ እግዚአብሐየርን መፍራ በረከቷ እግዚአብሀየር እንደ ፈጠራት እንደ ገነት ናት ተድላ ደስታና ክብርም በሷ አለ፡፡
፳፰. ልጄ በጉልበት ሳለህ ልመናን አትውደዳት ከመለመን ሞት ይሻላል፡፡ 
፳፱. የሌላ ማዕድ ደጅ የሚጠና ተስፋ የሚያደርግ ሰው አነዋወሩ እንደ ሞተ ሰው ነው እንጂ እንደ ደህነኛ አይደለም የሰው እህል የሚወድ ሰው ከሐሜት አይድንም የተመከረ አዋቂ ሰው ግን ከሁሉ ይጠበቃል፡፡ 
፴. ለማያፍር ሰው አፍ ልመና ያማረ ነው በሆዱ ግን አሳት ትነዳለች፡፡