፩. የፍፁም
ኃይል ፈጣሪ አቤቱ ቅር ብለህ ከመዓት ወደ ምሕረት ተመለስልን፡፡
፪. በአሕዛበ
ሁሉ አንተን መፍራት አሳድር፡፡
፫. ልዩ በሆኑ
ወገኞችንም ሥልጣንህን ግለጥ ኃይልህንም ይዩ፡፤
፬. እነሳቸው
የኛን ጥፋት ሲያዩ በኛ ጥፋት እንደተመሰገንህ እንደዚሁም ሁሉ እኛ የነሳቸውን ጥፋት ስናይ በነሳቸው ጥፋት ተመስን፡፡
፭. አቤቱ
ያላንተ ሌላ ፈጣሪ የለምና እኛ እንዳወቅንህ እነሱም ይወቁህ፡፡
፮. ታምራትህን
አሳይ ጌትነትህንም ግለጥ፡፡
፯. በሥልጣንህ
ኃይል በከበረ ሥልጣንህም
፰. ጥፋትን
አምጣባቸው መቅሠፍትንም አምጣ፡፡
፱. በደለኖችን
አጥፋቸው አንጥያኮስንም አጥፋቸው፡፡
፲. የባሮችህን
መሐላ አስብ የሚጠፉበትነም ቀን ፈጥነህ አድርጋት፡፡
፲፩. በእሳት
አጠፋቸው ከነሳቸው ያመለጡትንም በጦር አጥፋቸው በወገኖችህም ክፉ ያደረጉ ሰዎችን ሞት ያግኛቸው፡፡
፲፪. ያለኛ
ሌላ ሰው የለም የሚሉ የጠላቶችን አለቆችን ሥልጣን አጥፋ፡፡
፲፫ የያዕቆብን ልጆች ሁሉ ሰብስባቸው፡፡
፲፫ የያዕቆብን ልጆች ሁሉ ሰብስባቸው፡፡