፩. የሚጣፍጥ
እህልን በጎ ልቡናህን አይንቁትም ለበለጸግነት መትጋት ፈጽሞ ሰውነት ያከሳል ገንዘብህንም ማሰብ እንቅልፍ ያሳጣል፡፡
፪. የሚጠራጠሩት
ጠላት መኖርም በንጉልቻ እንቅልፍ ያስረሳል ጽኑ ቁርጥማት ያተጋል እንቅልፍም ያሳጣል፡፡
፫. ባለጸጋ
ገንዘብ ያደልብ ዘንድ ይዞራል ያረፈም ጊዜ በጥጋብ ደስ ይለዋል፡፡
፬. ድሀ ገንዘብ
በማጣት ይደክማል ባረፈም ጊዜ ወደ ልመና ይመለሳል፡፡
፭.ገንዘብ
የሚወድ ሰው አይጸድቅም ኃጢአትንም የሚዋት ሰው ይከተላታል፡፡
፮.ገንዘብ
ወደው የጠፉ ሰዎች ብዙ ናቸው ሞታቸውንም በፊታቸው አዩአት፡፡
፯. ገንዘብ
ለሚፈልጓት ሰዎች እንቅፋት ናት ሰነፍ ሰው ሁሉ በሷ ይሰነካከላል፡፡
፰. ከኋጢአት
ንጹሕ የሆነ ባለጸጋ ልቡናውንም ወደ ገንዘብ ያልወሰደ ባለጸጋ የተደነቀ ነው፡፡ ለወገኖቹ በጎ ነገር ያደረገ ማነው እንጃ
እናድንቀው፡፡
፲.በገንዘቡ
ያወቀበት ከሕግም ወጥቶ ያልሳተ ሰው ማነው እንጃ እናድንቀው እሱም መመኪያ ሆነው ኃጢአት መሥራት ሲቻው ኃጢአት የማይሠራ
ማነው፡፡
፲፩.ክፉ
መሥራት ሲቻለው ክፉ የማያደርግ ሰው ማነው እንጃ እናድንቀው በረከቱ ትጸናለች ምጽዋቱም በአሕዘብ አግር ትሰማ፡
የማዕድ ሥርዐት
፲፪.በታላቅ
ማዕድም ብትቀመጥ ለመብላት ጉሮሮህን አትክፈት፡ (ሁሉን ውጬው አትበል) በውሰጡም ብዙ ሥሩ አትበል
፲፫.ሰው ኣይን
ክፉ እንደ ሆነ አስብ ከሰው ዓይን የሚከፋ ምን አለ ስለዚህም ነገር የሰውን ዓይን ታላቅሳለች፡፡
፲፬.ላየኀው
ሁሉ አትሳሳ ዘእጅህን አትንከር ድስቱን ወዳንተ አትትት ድስቱን አንጥረግ፡፡
፲፭.ባልንጀራህ
ያቀረበልህን ሁሉ እወቅ ያቀረበልህንም ሁሉ ተረዳ፡፡
፲፮.ያቀረቡልህን
እንደ ብልህ ሰው ሁነህ ብላ ባልንጀራህን እንዳታስጸይፍ ስታላምጥ አፍህን አታጩህ፡፡
፲፯.ከሰው ሁሉ
አስቀድመህ ተው አትሳሳ እንደማይጠግብ ሰው አትሁን፡፡
፲፰.በሰው
መካከልም ብትቀመጥ እጅህን አስቀድመህ አታውርድ፡፡
፲፱.በመኝታህ
ሆድህን እንዳይከብድህ ጥቂት እንደሚበቃው እንደ አዋቂ ሰው መጥነህ ብላ፡፡
፳. ሰውነቱን
የሚመጥናት ሰው እንቅልፍ ጤና ነው ከእንቅል በጧት በተቀሰቀሰ ለጊዜ ሆዱን አይከብደውም ለማይጠግብ ለስሱ ሰው በሽታው ቁንጣን
ጓታና ብሰና ነው፡፡
፳፩. ትበላ
ዘንድ ግደ ቢሉህ ቀድመሃቸው ተነስ ከመብላትም እረፍ፡፡
፳፪. ልጄ
አድምጠኝ ምክሬንም አትናቅ ኋላ ነገሬን ታገኘዋለህ ምንም እንዳታጣ በሠረኸው ሥራ ሁሉ ደካማ አትሁን፡፡
፳፫. ለጋስን
ሰው በሥራው ማማር ይመርቁታል ንፉግ ሰውንም በክፉ ሥራው ይረግሙታል፡፡
፳፬. መጠጥ
ብዙ ሰዎችን አስቷቸዋልና ወይን በጠጣህ ጊዜ አትታበይ፡፡
፳፭. ጽኑ
ብረትን በወናፍ ይፈትኑታል እንደዚሁም ሁሉ የትቢተኞችን ልቡናቸውን ወይን ይፈትነዋል፡፡
፳፮. የሰው
ደግንነቱ ወይን መጠጣት ነው መጥኖ ለሚጠጣም ሰው ተድላ ደስታው ነው እሱ ለሰው ተድላ ደስታ ሊሆን ተፈጥሯልና ወይን ለማይጠጣ
ሰው ደህንነቱ ምንድነው፡፡
፳፯. ለልና
ፈጽሞ ተድላ ደስታ ነው ወይንን መጥኖፐ በጊዜው መጠጣት ደግ ነው፡፡
፳፰. ወይን
የልቡና ኃዘንን ያስረሳል ለሚያለቅስ ለሚያዝንም ሰው ወይን አጣጣው
፳፱. ሰነፍ
ሰው ወይን በጠጣ ከገዜ ክርክር ያበዛል ደስታል ይበድላል የመጠጥ ብዛት ኃይል ይሰጣል ቁስልም አያሳጣ፡፡
፴. ወይን
ጠጥቶ ሳለ ባልንጀራህን አትቁጣው ልቡናው ደስ ብሎት ሳለ አታሳዝነው የምትነቅፈውንም አትንገረው እሱ ሰክሮ ሳለ ጉዳይህንም
አትለምነው፡፡