ከኅጢአት ስለ መራቅ ጸሎት
1. አቤቱ
አባቴ የህይወቴ ፈጣሪ፤ በእነርሱ ምክር አትጣለኝ በእነርሱም እንዳልጠፋ አትለየኝ፤
2. ልቡናዬን
ማን በመከረልኝ ድንቁርናዬም ይተወኝ ዘንድ በተናገሩብኝም ነገር ድል እንዳይነሱ ለልቡናዬ ጥበብን ማን ባስተማራት፤
3. በደሌ
እንዳይበዛብኝ ኃጢአቴም እንዳይበረክትብኝ በጠላቶቼም ፊት እንዳልወድቅ ጠላቶቼም በእኔ ጥፋት ደስ እንዳይላቸው፤
4. ጌታዬ፣
አባቴ፣ የሕይወቴ ፈጣሪ ሆይ ዓይኔን የሚያስታትን ነገር አታምጣብኝ
5.
መጎምጀትንም ከእኔ አርቅልኝ፤
6. ጥጋብ አይምጣብኝ፣ ቁንጣንም አያቀናጣኝ ለክፉ ሰውም አሳልፈህ
አትስጠኝ፡፡
አንደበትን ስለ መግራት
7. ልጆቼ ሆይ
የአንደበቴን ምክር ስሙኝ ቃሌን የጠበቀ አይሰናካከልም አንደበቱን የጠበቀ አይወድቅም፡፡
8. ኃጢአተኛ
በስንፍናው ይያዛል፤ ተሳዳቢና ትዕቢተኛም በዚሁ ይሰነካከላሉ፤
9. ልጄ ሆይ
ለአፍህ መሐላን አታስለምደው፤ በማልህም ግዜ የቅዱሱን ስም በሐሰት አትጥራ፤
10. ሁል ግዜ እየተመረመረ የሚገረፍ ባሪያ ቁስሉ እንደማይደርቅ እንደዚሁ
ሲምል ሁል ግዜ የእግዚአብሔርን ስም በሐሰት የሚጠራ ሰው ከኃጢአት አይነጻም፡፡
12. ሞትን የምታመጣው ቃል አለች በያዕቆብም ርስት አትኖርም ይህ ሁሉ
በጻድቃን ዘንድ የለም በኃጢአትም አይሰነካከሉም፡፡
13. በውስጡ ብዙ ኃጢአት አለና ከአንደበትህ የመዘባበት ነገር አይውጣ፤
14. አባትህንና እናትህን አትስደባቸው፤ መኳንንቶችህንም አገልግል
በፊታቸውም አትሳት፤ ባልተወለድሁ እንዳትል የተወለድህበትንም ቀን እንዳትረግም በስንፍና እንዳትጠላ ሁን፡፡
15. በሰው
ላይ መሳለቅን የለመደ ሰው መላ ህይወቱን ብልህ አይሆንም፡፡
16. ኃጢአትን የሚያመጧት ሁለት ናቸው፤ ሶስተኛው ግን ሞትን ያመጣል፡፡
ቁጡ ሰውነት እንደሚቃጠል እሳት ናት እስክታሰጥመው ድረስ አትበርድም፤ በሰውነቱም የሚሰስን ሰው እሳትን እስኪያቀጣጥላት ድረስ
አይተውሰም፡፡
17. ለሴሰኛ
ሰው እህሉ ሁሉ ይጣፍጠዋል
19. ነገር ግን እንዳያየው የሰው ዓይንን ይፈራል፤ የእግዚአብሔር ዓይን
ከፀሐይ መቶ ሺህ ግዜ እንዲበራ የሰውንም ስራ ሁሉ እንደሚያይ ተሰውሮ የሚሰራንም ስራ እንደሚያውቅ አያውቅም፡፡
20. ሁሉም
ከመፈጠሩ በፊት በእርሱ ዘንድ የታወቀ ነው ከጨረሰም በኋላ እንዲህ ያደርገዋል፡፡
21. በከተማም
መካከል ይበቀለዋል ባልጠረጠረበትም ቦታ ያጠፋዋል፡፡
22. ባሏን
ትታ ምትሔድ ሴት እንዲሁ ናት፤ ከሌላ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤
23. በእግዚአብሔር አንዲት ክህደት አደረገች፤ ሁለተኛም ባሏን ከዳችው፤
ሶስተኛም በሴሰኝነቷ ሰረቀች፤ ከሌላ ወንድም ልጅን ደወለደች፡፡
24. እንዲህ
ያለችው ሴት ትዋረዳለች በልጆቿም ትገረፋለች፡፡
25. ዘሮቿ
ይጠፋሉ ቅርንጫፎቿም አያፈሩም፡፡
26. ስም
አጠራሯም የተረገመ ይሆናል ለቤቷም መርገምን ታወርሳለች መርገሟ እና ውርደቷም ለዘላለሙ አይጠፋም፡፡
27. ያያት
ሁሉ እግዚአብሐየርን ከመፍራት የሚበልጥ የእግዚአብሐየርንም ህግ ከመጠበቅ የሚጣፍጥ እንደሌለ ያውቃል፡፡