ሰነፍ እና ስንፍና
፩ ሰነፍ ሰው
በተቀመጠበት ቦታ እንደ ዋሻ ደንጊያ ነው በጽኑ ስንፍናው ሁሉን ያቦዝናል::
፪ ፫ ሰነፍ
ሰው በተኛበት ቦታ እንደሚያጸይፍ ፈረስ ነው:: የገደለው ሰው ሁሉ የጁን ትቢያ ማራገፉ ነው:: ያልተማረ ልጅ ላባቱ እፍረት
ነው ሰነፍም ልጅ የጎሰቆለች ትሆናለች::
፬ ብልህ ሴት
ልጅ ባሏን ትወርሰዋለች ሰነፍ ልጅ ግን ላባቷ ኅዘን ናት::
፭ ሁለጊዜ
ሰባት እጥፍ ጉስቁልናን ትጎሰቁላለች አባቷንም ታሳፍራለች ባሏንም ታሳፍራለች ደፋርም ናት::
ጥበብ እና ሞኝነት
፮ ባገኘበት
ቦታ ነገሩን የሚናገር ሰው በልቅሶ ቤት መሰንቆ እንደሚመታ ሰው ነው:: ግርፋት ከቁጣ ጋር ሁልጊዜ ብልህ ያደርጋል::
፯ ሰነፍ ሰውን
የሚያስተምረው ሰው የተሰበረ ገልን እንድ እንደሚያደርግ ሰው ነው የተኛ ሰውን ከጽኑ እንቅልፍ ቀስቅሰው::
፰ ለሰነፍ ሰው
የሚናግር ሰው ለተኛ ሰው እንደሚነግር ሰው ነው ተናግረኸው ከጨረስክ በሁዋላ ምን ተናገርህ ይልሃል::
፱ ተድላ
ደስታው አልፏልና ለሞተ ሰው አልቅስለት አእምሮው ጠፍቷልና ለሰነፍ ሰውም አልቅስለት::
፲ ከሞተ በኋላ
አይመለስምና ለሞተ ሰው ታለቅስለት ዘንድ አግባብ ነው:: ከመሞቱ መኖሩ ይከፋበታልና ለሰነፍ ሰው ግን በሕይወት እያለ
አልቅስለት::
፲፩ ለሰነፍ
ሐጥያተኛ በሕይወት በኖረበት ዘመን አልቅስለት::
፲፪ ከሰነፍ
ሰው ጋር ነገር አታብዛ አእምሮ ከሌለውም ሰው ጋር አትኑር ወደ መከራ እንዳያገባህ አንተም በሱ ስንፍና እንዳትነቀፍ ተጠበቅ::
፲፫ ከሱ ራቅ
ሰውነትህም ታርፋለች ይቀልሃል በሱ ስንፍናም አንተ የምትጎዳው የለም::
፲፬ ከአረር
የሚከብድ ምን አለ ሰነፍ ከመባልስ በቀር የሚከፋ ምን አለ::
፲፭ ከሰነፍ
ሰው ጋር ከመኖር ጨውና አሸዋ የብረት ወገን ናስንም ብትሸከም ይሻላል::
፲፮ ማገሩ
ያማረ በካብ ላይ ያለ ካቡ በተናደ ጊዜ ማገሩ እንዳይፈታ ያዋቂ ሰው ምክርም በጽኑዕ ልቡና እንደሱ ነው::
፲፯ ሁል ጊዜ ጽናቱ
ማገር ነው በግድግዳ ላይ ያሸዋ ምርግ እየተቀረፈ እንዲወድቅ::
፲፰ በነፋስ
ፊት ያለ ገለባም ነፋስ በነፈሰ ጊዜ እንዳይቆም የሰነፍ ሰውም አሳብ የሰደበው ሰው ቢኖር ቆሞ የማይዋጋ በፈሪ ሰው ልቦና ዘንድ
እንደሱ ነው::
፲፱ አይኑን
የጠነቆሉት ሰው እንባውን ያወርዳል ልቡናውንም በትምህርት ያደሰ ሰው ጥበብን ያሳያል::
፳ በወፎች
ደንጊያ የወረወረባቸው ሰው ያባርራቸዋል በወዳጁም የሚለገድ ሰው ወንድሜ ማለትን አጠፋ::
፳፩ በወዳጅህ
ሰይፍን ብትመዝ አፍህንም በሱ ከፍና ዝቅ አድርገህ ብትናገር ወዳጅ እንደሚሆንን መጠን ተስፋ አትቆርጥለትም::
፳፪
ብትለገድበት አፍህንም በሱ ክፉና ዝቅ አድርገህ ብትናገር ብትሰድበው ምክሩንም ብታወጣበት ብትከዳው ብታሳዝነውም ነው እንጂ
ወዳጅ እንድሚሆንህ መጠን ተሰፋ አትቁረጥለት በዚህ ነገር ወዳጅ ሁሉ ይሸሻል::
፳፫ አንተም ድሀ ብትሆንም በተድላው በደስታው ጊዜ ከሱ ጋራ ደስ ይልህ ዘንድ
ከባልንጀራህ ጋራ ሃይማኖትህን ጠብቅ ርስቱን ባገኘ ጊዜ ከሱ ጋራ ደስ ይልህ ዘንድ ቢቸገርም ከሱ ጋራ መከራውን ታገሥ::
፳፬ የእሳት
የጪሱ ተንታ ይቀድማል እንደዚሁም ደም ከማፍሰስም ጠብና ክርክር ይቀድማል::
፳፭ ወዳጄን
መሰወር አላፍርም ከፊቱም አልሠወርም::
፳፮ ነገር ግን
ስለሱ መከራ ብታገኘኝ የሰማ ሁሉ ሰሱ ራሱን ይጠብቅ::
፳፯ ላንደበቴ
ጠባቂ ማን ባኖረልኝ በነሳቸው እንዳልጠፋ አንደበቴም
እንዳትገድለኝ ባንደበቴ የጥበብን ቁልፍ ማን ባኖረልኝ::