ስለ ልጆች
፩፤የውሉዱን፣ነገር፣የሚናገር፣አንቀጽ፣ይህ፣ነው::ልጁን
የሚወድ፣ሰው፣በሱ፣ደስ፣ይለው፣ዘንድ፣ልጁን፣መቅጣትን፣ቸል፣አይልም::
፪፤ልጁን፣ያስተማረ፣ሰው፣በልጁ፣መናገር፣ያመሰግኑታል
በወዳጁም፣ዘንድ፣መመኪያ፣ይሆነዋል::
፫፤
ልጁን፣ያስተማረ፣ሰው፣ጠላቱን፣ያስቀናዋል፣በወዳጆቹም ዘንድ፣በልጁ፣መማር፣ደስ፣ይለዋል::
፬፤ከሱ፣በኋላ፣እንደሱ፣ያለ፣ልጅ፣ተክቷልና፣አባቱም፣ቢሞት
እንዳልሞተ፣ይሆናል::
፭፤ለጠላቶቹ፣የሚመክት፣ለወዳጆቹ፣የሚፈተፍት፣ከሱ፣በኋላ
እንደሱ፣ያለ፣ልጅ፣ተክቷልና::
፮፤በሕይወቱም፣ሳለ፣በልጁ፣ደስ፣ብሎታልና፣ቢሞትም፣ልቡ
አያዝንም::
፯፤ከልቅሷቸው፣የተነሣ፣ሰውነትህ፣ይነዋወጣልና፣ልጆችህን
ስለማስተማር፣ልቡናህን፣አሳዝን::
፰፤
ያልተገራ፣ፈረስ፣ገርጋሪ፣ይሆናል፣ያልተማረ፣ልጅም አውታታ፣ሆኖ፣ያድጋል::
፱፤
ልጅህን፣ካቀማጠልከው፣ይበረታታብህ፣ዘንድ፣ወደ መበርታት፣ይመለሳል፣ከሱም፣ጋራ፣ብትጫወት፣ያሳዝንህ ዘንድ፣ወደ፣ማሳዘን፣ይመለሳል::
፲፤
እንዳያሳዝንህም፣አትሳቅለት በፍጻሜ፣ዘመንህም ጥርስህን፣ያረግፍሃል::
፲፩ ፤
በጒልማስነቱ፣ሳለ፣ልጅህን፣አትቅጣው::
፲፪፤
ባደገ፣ጊዜ፣እንዳይከዳህ፣በልጅነቱ፣ጐን፣ጐኑን፣ግጠበው::
፲፫፤
በሱ፣ጥፋት፣አንተ፣እንዳታፍር፣ልጅህን፣አስተምረው ያገለግልሃል::
ስለ ጤንነት
፲፬፤
ሰውነቱ፣ከታመመ፣ሆዱ፣ከታሠረ፣ባለጸጋ፣ሰውነቱ ጤነኛ፣የሆነ፣ሆዱ፣የተከፈተ፣ድሀ፣ይሻላል::
፲፭፤
ሰውነትህ፣ጤነኛ፣ይሁን፣ሆድህም፣የተከፈተ፣ይሁን፣ከገንዘብና፣ከባለጸግነት ሁሉ ይህ ሰውነቱ፣ጤነኛ፣የሆነ፣ድሀ ይሻላል::
፲፮፤
በጤና፣ከመኖር፣ባለጸግነት አይወደድም ከልቡና፣ተድላ ደስታም፣የሚሻል፣ሌላ፣ተድላ፣ደስታም፣የለም::
፲፯፤
ከማያልፍ፣ችጋር፣ከቊርጥማትም፣በሽታ፣ሞት፣ይሻላል::
፲፰፤በተዘጋ፣አፍ
ፊት የቀረበ፣መብል ደስ እንዳያሰኝ፣እንደዚሁ ወደ መቃብርም እህልን የሚወስድ ሰው ደስ አያሰኝም::
፲፱፤ እነሳቸው
አይበሉ አይጠጡ አያሸቱ ለጣዖቶች መሥዋዕት መሠዋት፣ምን ይጠቅማል እግዚአብሔርም በደዌ የቀሠፈው ሰው እንደዚሁ ነው::
፳፤ጃንደረባ፣ቆንዦይቱን
ባቀፋት ጊዜ እንዲያዝን ባይኖቹ እያየ፣ያዝናል::
፳፩፤ ልቡናህን
የብስጭት ኅዘን አታሳዝን ሰውነትህንም፣አታበሳጭ::
፳፪፤የልቡና፣ተድላ
ደስታ፣ለሰው ሕይወቱ ነው የልቡና ተድላ፣ደስታም፣ዘመንን፣ያበዛል::
፳፫፤ሰውነትህን፣አለዝባት
የብስጭት ኅዘን፣ብዙ ሰዎችን አጥፍቷቸዋልና፣የብስጭት ኅዘንን የምትጠቅመውም የለምና የብስጭት ኅዘንን ካንተ፣ታርቅ ዘንድ
ልቡናህንም አረጋጋት::
፳፬፤ ቊጣና
ቅናት በሕይወት የሚኖርበትን ዘመን፣ያሳንሳሉ የብስጭት፣ኅዘንም ጊዜው ሳይደርስ ያስረጃል::
፳፭፤ አጫጅን
እየተከተለ የሚቃርም ሰው ማታ፣በራት እንዲተካከል እኔም፣ከነቢያት በኋላ፣ተነሥቼ በእግዚአብሔር፣ረድኤት ከነቢያት ማዕርግ
ደረስኩ::
፳፮፤ ይራቀቁ
ዘንድ ለሚወዱ ሰዎችም ሁሉ ነው እንጂ የደከምኩ ለኔ ብቻ፣እንዳይደለ እነሆ፣አስተውሉ::
፳፯፤ በሕዝቡ
ላይ የተሾማችሁ መኳንንት ስሙኝ የአሕዛብም አለቆች፣አድምጡኝ::
፳፰፤ ሚስትህና
ልጅህን ወዳጅህና፣ወንድምህንም አንተ በሕይወት ሳለህ፣በገንዘብህ አታሠልጥናቸው ኋላ፣እንዳትጸጸት በቤትህም ባዕድ አትሹም
ትለምናቸው ዘንድ ወደ መለመን እንዳትመለስ፣በሕይወት ሳለህ፣በገንዘብህ፣ላይ አታሠልጥናቸው::
፳፱፤አንተ፣በሕይወት
ሳለህ አእምሮህም ሳለች ግብርህን አትለውጥ::
፴፤አንተ፣የልጆችህን
እጅ ደጅ ከምትጠና፣ልጆችህ አንተን ቢለምኑህ፣ይሻልሃል::
፴፩፤በሠራኸው፣ሥራ፣አዋቂ፣ሁን፣በሾሙሁም፣ቦታ፣ሁሉ
ራስህን፣አታዋርድ::
፴፪፤በሕይወት፣የኖርህበት፣ዘመንህ፣ሁሉ፣ባለቀ፣ጊዜ
የምትሞ ትባትም፣ቀን፣በደረሰች፣ጊዜ፣የዚያን፣ጊዜ፣ገንዘብህን፣አውርስ::
፴፫፤
አህያህን፣ገለባ፣አብላው፣ጫነው፣ባለንጋ፣ባኮርባጅ ግረፈው፣ቅጣው፣መግበው፣ግዛው::
፴፬፤ባሮችህን፣ግዛቸው፣ዕረፍት፣ታገኛለህ፣ብታቦዝናቸው፣ግን፣ይከራከሩህ፣ዘንድ፣ካንተም፣ነጻ፣ይወጡ፣ዘንድ፣ይወዳሉ::
፴፭፤ቀንበር፣መጫን፣አንገትን፣ዝቅ፣ያደርገዋል፣ክፉ፣ባሪያንም፣አለንጋ፣እግር፣ብረት፣ያለዝበዋል::
፴፮፤ባሪያህን፣ግዛው፣ቦዘን፣ብዙ፣ክፋትን፣ታስተምራለችና::
፴፯፤አቦዝነህም፣አታኑረው::
፴፰፤የሚችለውን
ያህል፣ሥራውን፣ስጠው፣ባይገዛ፣ግን፣እግር ብረቱን፣አጽናበት፣ያለ ምክር፣የምትሠራው፣ሥራ፣አይኑር
ነገር፣ግን፣ሥጋዊውን፣ደማዊውን፣ሁሉ፣አትመነው::
፴፱፤ደግ፣ቤተ፣ሰብእ፣ቢኖርህ፣እንደ፣ወንድምህ፣አድርገው
እንደ፣ሰውነትህም፣ ውደደው::
፵፤ክፉ፣ነገር፣ብታደረግ፣ግን
ይኮበልልብሃል፣ያመልጥሃል ከዚህ፣በኋል በየት ጎዳና፣ታገኘዋለህ::