የዕለት የሕይወት መመሪያ
፩ ገንዘብህን በከንቱ አትበትን ገንዘብ በቃኝ አትበል::
፪
የሰውነትህን ፈቃድ አትከተል::
፬
እግዚያብሔር ብዙ ዘመን ይታገሣልና ኃጥያት ሰርቼ ፍዳ አልተቀበልሁም አትበል::
፭
ስለ ሐጥያት ንሰሐ መግባትን አትፍራ የእግዚያብሔር ቸርነቱ ብዙ ነው እያልክ በሐጥያት ላይ ሐጥያትን አትስራ::
፮ ቸርነትም መቅሠፍትም ከርሱ ዘንድ ይመጣልና መቅሰፍቱ በኃጢአተኛ ሰው ላይ ይመጣል::
፯
ለእግዚያብሔር መገዛትን ቸል አትበል ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ ፍዳህ ከመቅሠፍት ጋር በመጣብህ ግዜ በመከራ ትጨነቃለህ::
፰ በመከራህ ጊዜ አንተን ማዳን አይችልምና ቀምተህ ላመጣኸው ገንዘብ አትሳሳ::
ራስን ስለ መግዛትና ግልጽ ስለ መሆን
፱ ለሰው ሁሉ ምሥጢርህን አታውጣ:: የወደድኸውን ሁሉ አትከተል ላንዱ እውነት ላንዱ አሰት እንደሚናገር እንደ ኃጥአተኛ ሰው አትሁን::
፲ አንተስ በጥበብ ጸንተህ ኑር ቃልህም አንድ ይሁን::
፲፩ ፈጥነህ ስማ ቃልን ለመመለስ ግን የታገሥህ ሁን::
፲፪ ጠላቱን እስክታፈራለት ድረስ እስክታስገርምለት እስክታስደነግጥለት እስክትቀሥፍለት እስክታስተምረው ድረስ ደርሳ ሰውነቱንም እስክታስገዛለት ድረስ ደርሳ ከሱ ጋራ ጸንታ ትኖር ዘንድ አስቀድማ ትሰጠዋለች ከዚህም በዃላ ግን ቢተዋት ትቀበለዋለች ምክሩንም ትገልጥለታለች ከሷ ወጥቶ ቢሄድ ግን ትለየዋለች በሚገናኘው በጠላቱም እጅ ትጥለዋለች::
፲፫ እምትነግረው እንዳለ ለባልንጀራህ ንገረው የምትነግረው ነገር ከሌለ ግን እጅህን ባፍህ ላይ አድርገህ ዝም በል::
፲፬ መከበርህና መዋረድህ ከቃልህ የተነሣ ነው:: የሰው መከራው ባንደበቱ ከተናገረው ነገር የተነሣ ነው::
፲፭ አሚተኛ አትሁን ባንደበትህ አውታታ አትሁን የሌባ እፍረቱ ጥቂት ነው:: ልቡናው ሁለት ነገር የሚያስብ ሰው ግን መከራው ጽኑ ነው:: በታላቁም በታናሹም ሰው ዘንድ ቸር ሆነህ ተገለጥ::