፩. አለቃም
አድርገው ቢሾሙህ ራስህን አታኩራ ከነሳቸው አንዳንዱ ሁሉ አዘናቸውንም እዘን ተቀምጠህም ፍረድላቸው፡፡
፪.ፍርድህን
ጨርሰህ እረፍ መልክትህንም ጨርሰህ የክብር ዘውድን ታኝ ዘንድ ከሳቸው ጋራ ደስ ይልህ፡፡
፫.ሽማግሌ
ይገባሃል ተናገር ለበጎ ነገር ቸል አትል የጥበብህንም ነገር ተናገር፡፡
፬.ለመረመረህ
ሰው ሁሉ ምሥጢርህን አትናገር አንዳገኘህም አትራቀቅ፡፡
፭.በውርቅ ጌጥ
ያለ የከበረ ዕንቁ ያማረ የተወደደ እንደ ሆነ ዘፈንም ወይን በሚጠጡ ሰዎች ዘንድ እንደዚሁ ያማረ እንደ ሆነ መሰንቆና ዘፈንም
እንደሱ በመጠጥ ቤት ያማረ የተወደደ ነው፡፡
፮. ጉልማሳ
ካሰናበቱህ ተናገር በጭንቅ ተናገር ዳግመኛም ቢጠይቁህ፡፡
፰.አንድ ጊዜ
ተናግረህ ዚያን ጊዜ ነገርህን ጨርስ እያቅህም ባንደበትህ ዝም በል፡፡
፱.በመኳንንት
መካከል አትቀመጥ ሌላ ሰው ሲናገር ነገርህን አትናገር
፲. መብረቅ ከነጐድግድ በፊት እንደሚሮጥ እንዲሁ የሚያርፍ ሰው መከበሩ ከፊቱ ነው፡፡
፲፩. ወደ
ቤትህ ገብህ ሁሉን በጊዜው ጊዜ መጥህ አድርግ በዚያም ደስ ይልህ ተጫወት፡፤
፲፪. የሚገባውን
የሚወደደውን ሁሉ አድርግ ትእቢትን ነገር እንዳትናገር እወቅ በቃልህም አትበድል፡፡
፲፫. ከዚህ
ሁሉ ጋራ ፈጣሪህን አመስግነው እሱም ከበረከቱ ሁሉ ያጠግብሃል፡፡
ሕግን መተርጐም
፲፬. እግዚአብሔርን
የሚፈራ ሰው ለሕጉ ይገዛል ወደሱም ፈጥነው የሚሄዱ ሰዎች ፈቃደቸውን ያገኛሉ፡፡
፲፭. ሕጉንም
የሚጠብቀው ነው ሕን ከመጠበቁ የተነሣ ይጠግባል የሚጠራጠር ሰው ግን በሱ
ይፈፋል ይስታል፡፤
፲፮. ለሚፈሩት
ሰዎች መአውግዚአብሔር ይፈርድላቸዋል በፍላ ባለጸግነትም ሳሉ ጠላታቸውን ተበቅ ያጠፋላቸዋል፡፡
፲፯. ኃጢአተኛ
ሰው ግን የሚመክሩትን ሰዎች አይስማም መሁሉም እደ ልቡ ይመስለዋል፡፡
፲፰. ብልህ
ሰው ያለምክር የሚሠራው ሥራ የለም የሚያዝን ጠላት ትቢተኛ ያለምክር ሥራውን ሠርቶ ፍርሃትን ያደርጋል፡፡
፲፱.ልጄ አንተ
ግን ያምክር የመትሠራው፡፡ ሥራ የለም የሠራኸውንም ሥራ አታጥፋ፡፡
፳. በጥፋት
ድንጋይ እንዳተሰነካከል ፈጽመኅ በምድረ በዳ አትሑድ፡፡
፳፩. ጠላትህን
በምድረ በዳ አትመነው፡፡ በፈቃድህ ጸንቶ የሚኖር ልጅህን ስንኳ አትመነው፡፡
፳፪. በሠራኸው ሥራ ሁሉ ሰውነትህትን ደስ አሰኛት በሁሉም ትዕዛዙን ጠበውቅ፡፡
፳፬. ሕን
የሚጠብቅ ሰው የነመጻፉን ትዕዝ ይሰማል በአግዚአብሔርም ያመነ ሰው የሚያጣው ነገር የለም፡፡