1 ለበጎ ነገር
ሳይሆን የሚገሥጽ ሰው አለ፤ ዐዋቂ ሆኖ ሳለም ዝም የሚል ሰው አለ፡፡
2 ነገር ግን
ከመንቀፍ መገሠጽ ይሻላል፡፡
3 ስሕተቱን
የሚያምን ከጥፋት ይድናል፡፡
5 እያወቀ ዝም የሚል ሰው አለ፣ ንግግር በማብዛትም ራሱን የሚያስጠላ ሰው
አለ፡፡
6 የሚመልሰውን
አያቅምና ዝም የሚል ሰው አለ፤ ጊዜውንም እስኪያገኝ ድረስ ዝም የሚል ሰው አለ፡፡
7 ብልህ ሰውም
ጊዜውን እስኪያገኝ ድረስ ዝም ይላል፤ አላዋቂና ደፋር ሰው እንዳገኘ ይናገራል፡፡
8 ነገርን የሚያበዛ ሰውን ይቆጡታል፤ራሱንም የሚያኮራ ሰውን ይጠሉታል፡፡
9 ችግሩ
የሚያዋርደው ሰው አለ፤ ገንዘብም አግኝቶ የማይበረክትለት ሰው አለ፡፡
10 የማይጠቅምህን የሚሰጥህ ሰው አለ፤ ሰጥቶም እጥፍ አድርጎ የሚቀበልህም
ሰው አለ፡፡
11 እየተቸገረ
ራሱን የሚያኮራ አለ፤ ራሱን በማዋረዱም የሚከብርም አለ፡፡
12 በጥቂት
ብዙ የሚገዛ አለ፤ ሰባት እጥፍ ያደርገውም ዘንድ ይፈልጋል፡፡
13 ብልህ ሰው
በቃሉ ራሱን ያስወድዳል፤ የአላዋቂዎች ስጦታም ተወዳጅነት የላትም፡፡
14 አላዋቂ ሰው ጥቅምና ተወዳጅነት የሌለውን ገንዘብ ይሰጥሃል፤ ጥቂት
ቢሰጥህም ለልቡ ብዙ የሰጠህ ይመስለዋል፡፡
15 ጥቂት
ቢሰጥህ ብዙ እንደ ሰጠህ ይላገድብሃል፤ በአንተም ላይ ነገሩን ያበዛል፤ የሰጠኽንም ይናገርብህ ዘንድ በአደባባይ ይዞራል፤ ዛሬ
ቢሰጥህ ነገ ይከፈልሃል፣ እንዲህ ያለው ሰው የሚያስጠላ ነው፡፡
16 አላዋቂ ሰው ግን “ወዳጅ አልፈልግም ምን ይጠቅመኛል? በጎ ነገር
ያደርግሁለት እኔ ዋጋን አላገኝምና፤ እህሌንም የሚመገቡ ሰዎች በእኔ ክፉ ነገር ይናገራሉ፣
17 ሁሉም
ሁልጊዜ ያሙኛል፤ በእኔ ይስቃሉ” ይላል፡፡
የማይገባ ንግግር
18
በአንደበትህ አድጦህ ከምትወድቅ፣ በምድር ላይ አድጦህ ብትወድቅ ይሻላል፤ እንዲሁ የክፉ ሰው አወዳደቅ ፈጥኖ ይመጣል፡፡
19 እንዳገኘ
የሚናገር ሰው ራሱን ያስነውራል፤ ለቃሉም መወደድ የለውም፤ በአላዋቂዎች አንደበትም ነገር ይጠላል፡፡
20 በጊዜው
አይናገረውምና፣ በአላዋቂ ሰው አንደበት ምሳሌ ይጠላል፡፡
21 በተቸገረ
ጊዜ እግዚብአብሔርን ወደ መፍራት የሚመለስ ሰው አለ፤ ሰውነቱም በመልካም ታርፋለች፡፡
22 በማፈርም
ሰውነቱን የሚያጠፋ አለ፤ በአላዋቂነቱም ሰውነቱን ያጠፋል፡፡
23 በማፈር ላይሰጠው ለወዳጁ ተስፋ የሚሰጠው አለ፡፡ ስለዚህም ነገር
ከንቱ ጠላት ይሆነዋል፡፡
24 የሐሰተኛ
ሰው ውርደቱ ክፉ ነው፤ የአላዋቂዎች ነገራቸው የተጠላ ነው፡፡
25 ከሐሰተኛ
ሌባ ይሻላል፤ ነገር ግን የሁለቱም ፍጻሜያቸው ሞትና ውርደት ነው፡፡
26 ሐሰተኛ ሰው ፈጽሞ ይዋረዳል፣ ያፍራልም፡፡
27 በቃሉ
ብልህ የሆነ ሰው ነገሩ ይሰማል፤ ብልህ ሰው መኳንንቱን ደስ ያሰኛል፡፡
28 ምድርን
የሚያርሳት የእህሉን ክምር ያበዛል፤ መኳንንቱንም የሚያገለግል ራሱን ይጠቅማል፡፡
29 እጅ መንሻና መማለጃ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ አፋቸውን ያዘጋል፤
ቃላቸውን ያስለውጣል፡፡
30 የተሰወረ
ጥበብ እንደ ተቀበረ ወርቅ ነው፤ እንግዲህ የሁለቱስ ጥቅማቸው ምንድን ነው?
31 ጥበቡን
ከሚሰውር ብልህ ሰው፣አለማወቁን የሚሰውር አላዋቂ ሰው ይሻላል፡፡