፩፤
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ያደርጋል፥ ሕጉንም የሚጠብቅ ሰው ያገኛታል።
፪፤ እንደናቱ
ትከባከበዋለች፥ እንደ ቆንጆ ሴትም ትዋሐደዋለች።
፫፤ የጥበብን
እህል ትመግበዋለች፥ የእውቀትንም ውኃ ታጠጣዋለች።
፬፤
የሚጠብቃትም ሰው በመከራ አይወድቅም፥ የሚታመንባትም ሰው አያፍርም።
፭፤
ከባልንጀራው ይልቅ ታገነዋለች፥ በብዙ ሰዎች መካከልም ነገር ይናገራል።
፮፤ ተድላ
ደስታ ትሰጠዋለች፥ ተድላ ደስታ ያለበት ዘውድንም ታቀዳጀዋለች፣ ስሙንም ለዘለዓለሙ ያስጠራል።
፯፤ ሰነፎች
ግን አያገኟትም፥ ኃጢአተኞች ሰዎችም አያይዋትም።
፰፤ ከትዕቢተኞችም ሰዎች የራቀች ናት፥ አሰተኞችም አያስቧትም።
፱፤
እግዚአብሔርን በመፍራት የሚናገር አይደለምና ኃጢአተኛ ሰው ባንደበቱ የተናገረው ነገር ያማረ አይደለም።
፲፤ ምሳሌን
በጥበብ ይናገራታል፥ እግዚአብሔርም የሚማራትን ሰው ይረዳዋል።
፲፩፤ ስለ
እግዚአብሔር ብዬ ከሥጋ፣ ከጠጅ ተከለከልሁ አትበል፤ እሱ የጠላውንም አትሥራ።
፲፪፤ ኃጢአት ሠርተህ እሱ አሳተኝ አትበል፥ እግዚአብሔር የረከሰውን ሰው
ሁሉ ጠልቷልና፤ እሱስ ኃጢአተኛ ሰውን አይወድም።
፲፫፤ የሚፈሩትንም ሰዎች ይወዳቸዋል።
፲፬፤ እሱ
ቀድሞ ሰውን፥ በንጽሐ ጠባይዕ ፈጥሮ፤ በወደደው ሥራው ተወው።
፲፭፤ ትእዛዙን
ትጠብቅ ዘንድ፥ ሃይማኖቱንም ታጸና ዘንድ ብትወድ ግን ፈቃዱ ነው።
፲፮፤ እጅህን
በመረጥኸው ትጨምር ዘንድ እነሆ፦ እሳትና ውኃን አኖረልህ። (ጽድቅና ኃጢአትን)
፲፯፤ ሞትና
ሕይወትም በሰው ፊት ነው፥ ከነሳቸው የመረጠውን ሥላሴ ይሰጡታል።
፲፰፤
የእግዚአብሔር ጥበቡ ብዙ ነውና ዕውቀቱም የጸና ነውና ሁሉን ያውቃል፤ ሁሉን ያያል።
፲፱፤ ዓይኖቹም፥ የሚፈሩትን ሰዎች ይመለከታሉ፤ እሱም የሰውን ሥራ ሁሉ
ያውቃል።
፳፤ ኃጢአት ይሠራ ዘንድ እሱስ ያዘዘው የለም፥ ይበድልም ዘንድ ማንም ማን
አላሰናበተውም።