የደግ ሴት ተግባር
፩፤ ደግ ሴትን
ባሏ ያደንቃታል በህይወት የሚኖርበትም ዘመን እጥፍ ይሆናል ፡፡
፪፤ የበሬ
ወገን የሆነች ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች ዘመኑንም በደስታ በተድላ ይጨርሳል፡፡
፫፤ የደግ ሴት
እድሏ ያማረ ነው እግዚያብሔርንም የሚፈራ ሰውንም ወደ እድሉ ታደርሰዋለች ፡፡
፬፤ የባለጸጋውም የድሃውም ልቡ ያማረ ይሁን ሁል ጊዜም ፊቱ የበራ
ይሁን፡፡
ስለ ክፉ ሴት
፭፡ በእነዚህ
በሶስቱ ነገሮች ልቦናየ ደነገጠብኝ አራተኛውም ልቦናየን፡ አስፈራኝ ፡ይኸውም ያገር ወንጀል የ አህዛብ መሰብሰብ ሰውን ለሞት
የሚያደርስ አሰተኛ ምስክር ነው፡፡
፮ ባሏን
ከውሽማዋ ጋራ የምታቀና ሴት የልብ ቁስል ናት የሰውነትም ኀዘን ናት ፡በመከራው ሁሉ የነገረ ሠሪ አንደበት ከመጣው ግርፋት ጋራ
ትተካከላለች፡፡
፯ደረቅ ሴት
ውልቅ ውልቅ እንደሚል እንደበሬ ቀንበር ናት ከእሷም ጋራ የሚኖር ሰው ጊንጥ እንደሚጨብጥ ሰው ነው፡፡
፰፤ አፍረቷን
የማትሸፍን ሰካር ሴት ጽኑ ጥፋት ናት ፡፡
፱፤ የሴት
ዝሙቷ በ አይኗ ይታወቃል ፡ በቅንድቧም ይታወቃል፡፡
፲፤ ስታ
እራሷን እንዳታጠፋ ልጅህን አጥንተህ ጠብቃት፡፡
፲፩፤ የሚጎዳህ
ነገር ቢኖር ትጽጸት ዘንድ ወደመጸጸት እንዳትመለስ ከባሏም ፈቃድ እንዳትወጣ አድርግ
፲፪፤ የተጠማ ሰው ጭቃውን እንዲልስ ከቀረበውም ውኃ እንዲጠጣ በእንጨት
ስርም እንዲያርፍ ፡፡
፲፫፤ አርበኛ ፍላፃውን፡ ከጉራንጉሬው ፈጥኖ እንዲያወጣ ሰሰኛ ሴትም ከቤቷ
መዘዝ ብላ ፈጥና ትወጣለች፡፡
የደግ ሴት በረከት
፲፬፤ የሴት መወደዷ ባሏን ደስ ያሰኛል፡፡
፲፭፤ ጥበቧም
ሰውነቱን ያድሰዋል
፲፮፤ የዋህ ሴት ለእግዚያብሔር እድሉ ናት
፲፰፤ ሰውና
እግዚያብሔርን የምታፍር ሴት በበረከት ላይ በረከትን ታገኛለች፡፡
፲፱፤ ነገር
ለምትታገስ ሴት ለውጥ የላትም ፡፡
፳፤ ፀሐይ
እግዚያብሔር በፈጠረው ሰማይ ሆኖ እንዲያበራ እንዲሁ የደግ ሴት ጌጧ ባማረ በቤቷ ውስጥ ነው፡፡
፳፩፤ የደብተራ
ኦሪት ፋና በመቅረዟ ላይ እንድታበራ እንደዚሁ የብልህ ሰውም ግብሩ በመልኩ ይታወቃል፡፡
፳፪፤ በብር
ሰክተት ላይ የቆሙ የወርቅ ምሰሶዎች ደስ እንዲያሰኙ በበጎ ስራ ጸንቶ የሚኖር የደግ ሰው እግር አገባብም እንደዚሁ ደስ
ያሰኛል፡፡
፳፫፤ በነዚህ
በሦስቱ ነገሮች ልቦናየ አዘነብኝ ፡፡
፳፬፤ አራተኛው
ግን ብስጭትን አመጣብኝ
፳፭፤ መጀመሪያ
አርበኛ ጨካኝ የሆነ ሰው የሚበላው የሚጠጣው አጥቶ ቢቸገር ነው፡፡
፳፮፤ ሁለተኛም
አዋቆች የሆኑ ሰዎች ከእግዚያብሔር ህግ ወጥተው ቢስቱ ነው፡፡
፳፯፤ ሦስተኛው ጽድቅን ትቶ ወደ ሐጢያት የሚመለስ ነው፡፡
፳፰፤ እንዲህ
ያለውን እግዚያብሔር በጦር ያጠፋዋል፡፡
፳፱፤ አንጥረኛ
ከሐጢያት በጭንቅ ይድናል መሸተኛም ከሐጢያት ተመልሶ አይጸድቅም፡፡