፩. ሕጉን
የሚጠብቅ ሰው መባ ያገባል፡፡
፪. ትዕዛዙን
የሚሰማ ሰው ድህነቱ ሊደረግለት መሥዋዕት ይሠዋል፡፡
፫. ስንዴ
የሚያገባ ሰው ዋጋውን ይመልሳል፡፡
፬. ምጽዋት
የመጸወተ ሰው የምስጋና መሥዋዕትን ሠዋ፡፤
፭. የእግዚአብሔር ደፈቃዱ ኃጢአት እንዳትሠራ ነው ከበደልም ትርቅ ዘንድ ፈቃዱ
ነው፡፡
፮. ወደ
እግዚአብሔር ማደሪያ ወደ ቤተ ክርስቲያ ባዲህን አትግባ፡፡
፯. ይህ ሁሉ
ስ ትዕዛዙ አድርግ፡፡
፰. የደግ ሰው
ምሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል መዓዛውም ወደ እብዚአብሔር ይደርሳል፡፡
፱. የደግ ሰው
መስዋዕት የከበረ ነው ስም አጠራሩም ሁሉ አይዘነጋበትም፡፡
፲. ፊትህን
ደስ እያለህ እግዚአብሔርን አመስግነተው ከመጀመሪያ አዝመራህም አሥራት መግባተን አትተው፡፡
፲፩. የሰጠህን
ገንዘብ ሁሉ ፊትህን ደስ እያለህ ስጠው ደስ እያለህም ያዝመራህን አሥራት አግባ፡፡
፲፪. እንደ
ክብሩ ብዛት መጠት ለእግዚአብሔር መባህን አግባ በጅህ ካገኘኀው ገንዘብም ፊትህን ደስ እያለው አግባለቴ፡፡
፲፫. እግዚአብሔር ዋሃግን ይመልስልሃልና ሰባት እጥፍም አድር ይሰጥሃልና
ፊትህን ደስ እያለህ አግባለት
፲፭.እግዚአብሔር
የውት ዳኛ ነውና ፊትን አይቶም አያዳላምና የበደልን መስዋዕት የሚቀበል አይምሰልህ፡፡
፲፮. ይሐውንም
ስለ ችጋሩ ከባለጸጋው አይለየውም የተበደለ ሰውንም ጩኸት ይሰማል፡፡
፲፯. እናት
አባት የሞቱበት ልጅ ልመናን ቸል አይልም ባልቴት ሴትንም ያስለቀሳት ሰው ቢኖር
፲፰. እንባንም
በፊቷ ላይ ብታወርድ፡፡
፲፱. እንዚሁ
ባአለቀሰት ሰው ላይ አንባ ይወርዳል፡፡
፳. በውነት
የሚያገለግለውን ሰው ልመናውን ይቀባዋል ልመናውም ወደ እግዚአብሔር ትደርሳለች፡፡
፳፩. የድሀውም
ልመና ወደ አግዚአብሔር ትደርሳለች ወደሱ አስክትደርስ ደርሳ አትመለስም እግዚአብሔርም እስኪያያት ድረስ ደርሳ አትመለስም፡፡
፳፫. ለደጋግ
ሰዎች ይፈርድላቸዋል ጠላታቸውንም ተበቅሎ ያጠፋላቸዋል የጠላታቸውን ሥልጣን እስኪያጠፋ ድረስ ስለነሳቸው ፈጽሞ ቸል አይልም፡፡
፳፬. አሕዛብን
ተቀብሎ ያጠፋቸዋል፣ በደለኞችንም ሁሉ ያጠፋቸዋል የኃጢአተኞችንም ሥልጣን ያጠፋታል፡፡ ለሰው ሁሉ እንደ ሥራው ዋጋውን ይፍለዋል
የወገኖቹን በቀል ይመልሳልና በቸርነቱም ደስ ያሰኛቸዋልና፡፡
፳፭. ስለ
ሰዎችም ሁሉ እንደ ሥራቸው እንደ ሥራቸው ፍዳውን ይከፍላቸዋል፡፡
፳፮. ዝናም
ያዘ ደመና መበበረሃ ደስ እንዲያሰኝ በመከራው ጊዜ ከይቅርታን የሚያገኘ ሰው የተደነቀ ነው፡፡