Sunday, October 6, 2013

ምዕራፍ ፴፮




፩. ይፈጥኑት ዘንድ ነው እንጂ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውን መከራ አያገኘውም ከመከከራይቱም ይድናል፡፡ 

፪. ብልህ ሰው መጽሐፍ መስማትን ይወዳል የሚጠራጠር በመጽሐፌ የማያምን ሰው ግብ በጥልቅ ነፋስ መካል እንደምትጋጋለል መርከብ ይሆናል፡፡

፫. ብልህ ሰው አምኖ በእግዚአብሔር ሕግ ይዛል እግዚአብሔርም የታመነ ወዳጁ ይናል፡ ደስ ያሰኘዋል፡፡

፬.የምትግረውን ነገርህን አዘጋጅተህ አድምጥ የምታደርገውንም ምክንር አጸንተህ ተናገር፡፡ 

፭. የሰነፍ ሰው ልቡና እንደ ሠለረገላ መንኮሸከረከር እንዝር ነው፡፡ 

፮.የተጌራ ፈረስ እንደ መበጎ ወዳጅ ነው፡፡ 

፯. ባንዱ ዘመን የሚመላለሰው ቀን ሁሉ በፀሐይ ብርሃን ጸንቶ ሲኖር አንዲቱ ቀን ካንዲቱ ቀን በምን ትበልጣለች ቢሉ፡፡ 

፰.ቀኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ይለያል የበዓሉም ጊዜ በቁጥሩ ይታወቃል፡፡

፱. ከቀኑም ያከበረ ያገነነው አለ፡፡ ከነሳቸውም በየጊዜያቸውና በየቁጥራቸው አዝመራንና ክረምተን በጋን ለየ፡፡ 

፲. እኛ ሁላችን የዳም ልጆች ከመሬት ተገኘን አዳምም ከመሬት ተፈጠረ፡፡ 

፲፩. እግዚአብሔር በጥበቡ ብዛት ለያው በየሥራቸው አዘጋጃቸው፡፡ 

፲፪. ከነሳቸው መረቀው አለ ያገነናቸውም አሉ ከነሳቸው ለያቸወው አሉ የታያቸውም አሉ፡፡ ከነሳቸው የረገማቸቸው ያጎሳቆላቸውም አሉ አንደ ስራቸውም የቀነጀላቸውም አሉ፡፡ 

፲፫. እኛ በሱ ዘንድ ባክላ ሠሪ እጅ እንዳለ ጭቃ ነን ፍጥረቱ ሁሉ በሥራቱ ጸንቶ ይራል ሰውም በፈጣሪው ሥልጣን ጸንቶ ለይራል ሁሉንም እንደ ሥራው ይከፈለዋል፡፡ 

፲፬. የበጎ ሥራ ተቃኒዋ ክፍት ናት የሞትም ተቃራኒዋ ሕይወት ናት እንደዚህሁም የጸድቅ ተቃራኒዋ ኃጢአት ናት፡፡ 

፲፭. ከዚህ ሁሉ ጋራ የእግዚአብሔርን ፍጥረቱን ተመልከት አንዱም አንዱም በየወገኑ ለሁሉ ሁለት ሆኑ ተፈጠረ፡፡ 

፲፮.እኔ ግን ከሁሉ በኋላ ተነሥቼ ይኀን ነገር አሰብሑት ከጥንቱም ጀምሬ መረመርኩት፡፡

፲፯. በስምህ የተጠሩ ወገኖችህን አቤቱ ይቅርበል በበህር ልጅህ ያስመሰልቻው እስራኤልንም ይቅር በል፡፡

፲፰.የምትመሰገንባት ቤተ መቅደስን በረድኤት የምታድርባት አገርህ ኢየሰሩሳሌምንመን ይቅር በው፡፡

፲፱. በጽዮችንም የቃልህን ረድኤት አሳድርባት ረድኤትንህንም በወገኖች አሳድር፡፡

፳.አስቀድሞ ለፈጠረካቸው ሰዎች ሕግህን አስተነምራቸው ለነቢያትም ስምህን አጽና፡

፳፩. አገልጋዮችህ ነቢያትን ያምኗቸው ዘንድ ተስፋ ላደረጉህ ለመቃብያን ዋጋቸውን ስጣቸው፡፡ 

፳፪. አቤቱ የባሮችህንና የነነቢያትን ጸሎታቸውን ስማ የአሮንንም በረከት በወገኖችህ አሳድር በዚህ ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ለዘላለሙ ፈጣሪ አግግዚአብሔር አንተ ብቻ እንደሆንክ ይወቁ፡፡

፳፫. እህል ሁሉ ይበላል ወደ ሆድ ይወርዳል ነገር ግን 

፳፬. ከህል የሚጣፍጥ እህ አለ፡፡ እንዲም ሁሉ ያዋቂ ሰው ልቡና አሰት ነገርን ይለያል፡፡

፳፭.  ክፉ ልቡና አሰት ነገርነ  ያስባል ብዙ መከራ የተቀበለ ሰውም ትዕግሥትን ይለምደዋል፡፡

፳፮. ወንድ ሁሉ ሚስት አገባሁ ይላል ነገር ግን ከሴት የምትበልጥ ሴት አለች፡፡ 

፳፯. የሴት መልኳ ፊቷን ያበራዋል ከሰው ሁሉ ፈቃድ እሷ ትበልጣለች፡፡ 

፳፰. የዋህ ብትሆን ቃሏም ያማረ ቢሆን በሏ እንደ መልአክ ነው እንዲ እንደ ሰው ይደለም፡፡

፳፱.  ረዳቱ ናትና ጽኑ መጠጊያምውም ናትና ልባም ሴትን ያባ ሰው ተድላ ደስታውን አገኘ፡፡

፴. ቅጥር የሌለው ቤት ገንዘቡ እንዲሠረቅ እንደዚሁ ሚስም የሌለው ሰው ጠጨንቆ ይራል፡፡ 

፴፩. ካነድ አገር ወዳንዱ አገር የሚሰደድ ሌባን የሚዋሰው የለም ንብረትና ቤት የሌለው በመሸበት የሚያድር ሰውንመ እንደዚሁ የሚዋሰው የለም፡፡